Saturday, 06 March 2021 13:53

የተጓዡ ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም “ሀገሬን” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     የእውቁ ተጓዥ ጋዜጠኛ  ሔኖክ ስዩም ሶስተኛ ስራ የሆነው “ሀገሬን  መፅሐፍ ለንባብ በቃ። መፅሐፉ በዋናነት ጋዜጠኛው ተራራ እየቧጠጠ፣ ቁልቁለት እየተንሸራተተ የወጣና የወረደባቸውን በአራቱም የሀገራችንን አቅጣጫዎች ያያቸውን፣ የዳሰሳቸውን፣ የተመሰጠባቸውን፣ የተደመመባቸውን የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን፣ ባህላችንን፣ መለያችንን፣    ስነ-ልቦናችንን አጠቃላይ ማንነታችንን እንደ መስታዎት ለህዝብ ያሳየበት የጉዞ ማስታወሻ ስብስብ ነው።
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ያያቸውን ሀቆች ከታሪክ ጋር እያጣቀሰ ዋቢ መፅሐፍትን እየጠቀሰ የሰነዳቸው የጉዞ ማስታወሻ ታሪኮች በቀጣይ ለሚጓዙ፣ ለሚመራመሩና የማወቅ ፍላጎት ላላቸው ጥርጊያ መንገድም ሆኖ ያገለግላልም ተብሏል። በ259 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ190 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ጋዜጠኛው ከዚህ ቀደም “የመንገድ በረከት” እና “ጎንደርን ፍለጋ” የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም።

Read 11158 times