የአምባሳደር ዲባባ አብደታ (ዶ/ር) “የዲፕሎማቱ ማስታወሻ- ከእረኝት እስከ አምባሳደርነት” የተሰኘ ግለ-ታሪክ መፅሀፍ በትላንትናው ዕለት ተመርቆ። መፅሀፉ የዕውቁ አምባሳደር ዲባባ አብደታን ከልጅነት አስከ ዕውቀት፣ ከእረኝነት እስከ አምባሳደርነት የሚዘልቅ የሕይወት ጉዙ ያስቃኛል፡፡ “የዲፕሎማቱ ማስታወሻ”፤ባለታሪኩ በትምህርትና በስራ ዓለም የተጓዙበትን ውጣ ውረድና ስኬት በውብ ቋንቋና በማራኪ አገላለጽ ይተርካል፡፡
በ15 ምዕራፎች ተደራጅቶ በ440 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ250 ብርና በ50 ዶላር ለገበያ ቀርቧል።