Saturday, 13 March 2021 12:13

Epilepsy...የሚጥል ሕመም… March /26…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(3 votes)

 ምስሉን የምትመለከቱት ሪቫን በላዩ ላይ Epilepsy የሚል ጽሁፍ ያለበት ሲሆን ቀለሙም የወይን ጠጅ ነው፡፡ ይህ ምልክት በየአመቱ የሚጥል በሽታን Epilepsy በሚመለከት በአለም አቀፍ ደረጃ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የንቃተህሊና ማዳበሪያ ስራዎች ለመስራት እንዲያስችል ሰዎች በደረታቸው ላይ አድርገው እንዲንቀሳቀሱ የሚረዳ ነው፡፡
የሚጥል በሽታ በአለማችን ወደ 65 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን የሚጎዳ ሲሆን Cassidy Megan በተባለ የዘጠኝ አመት ካናዳዊ ልጅ በ2008/እ.ኤ.አ ምልክቱ የወይን ጠጅ የሆነ ሪቫን አለም አቀፍ ምልክት ሆኖ እንዲያገለግል መረጠ፡፡ ይህም ምርጫ Epilepsy Association of Nova Scotia (EANS) በተባለ ድርጅት በመታገዙ ወይም ይሁንታን በማግኘቱ ምልክቱ አለም አቀፍ እንዲሆን ተወሰነ። በየአመቱም March 26 አለም አቀፍ የEpilepsy ቀን ተብሎ በመታሰብ ላይ ይገኛል፡፡
March 26 አለምአቀፍ የEpilepsy ቀን በየአመቱ ሲታሰብ በሕመሙ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን ፍርሀትና በህብረተሰብ ዘንድ በሕመሙ ዙሪያ በዘልማድ ሰለሚነገሩ ነገሮች ያለውን ግንዛቤ ለመለወጥ የሚያስችሉ ስራዎች እንዲሰሩ የሚያግዝ እለት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ይህ በየአመቱ የሚከበር የEpilepsy ቀን  ሕመሙ ባለባቸው ሰዎች ላይ ሊኖር የሚችለውን አድሎና መገለል ለማስወገድ እና በህመሙ የተያዙት ሰዎች ከምንም ጉዳይ ወደሁዋላ ሊባሉ የማይገባቸው፤ ተገቢውን እውቅናና ክብር የማይነፈጉ መሆናቸውን ለማሳየትና እውነታውን ለማሳወቅ እንዲረዳ በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ስራዎች የሚሰራበት ቀን ነው፡፡ ስለዚህም እ.ኤ.አ March 26 ሁሉም ሰዎ የወይንጠጅ ምልክቱን በደረቱ ላይ በማድረግ ወይንም የወይን ጠጅ ቀለም ያለው ልብስ በመልበስ እለቱን በአለም ላይ ላሉ በህመሙ ለሚሰቃዩ 65 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ደህንነት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ማሰብ እና መነጋገር እንዲሁም የተሻለ እርምጃ ለመውሰድ ይረዳል፡፡  
WWW.epliepsyscotland.org.uk የተባለው ድረገጽ ከሚጥል በሽታ ጋር በተያየዘ የሚከተሉትን የጉዳት አይነቶች ዘርዝሮአል፡፡
የሚጥል በሽታ በድንገት አእምሮን የሚያዛባ ህመም ሊባል ይችላል፡፡ ሕመሙ ያለባቸው ሰዎች የሚከተሉት ስሜቶች ሊኖሩአቸው ይችላል፡፡  
የአእምሮ መሳት፤
ለአደጋ መጋለጥ፤
በራስ የመተማመን ብቃትን መቀነስ፤
የእራስን ማንነት ዝቅ አድርጎ መመልከት፤
እራስን አለአግባብ መፈረጅ፤
እራስን በተገቢው መንገድ አለመመልከት፤
የመንጃ ፈቃድ መያዝ አለመቻል፤
መድሀኒት አወሳሰድ ላይ የጎንዮሽ ጉዳት መከተል፤
ከማህበራዊ ኑሮ መገለል፤
እራስን ችሎ ከቤት ወደውጭ መውጣትን መፍራት፤
የሚጥል ሕመም የተለያየ አይነት ያለው ሲሆን አንዳንዱ በዘር ሐረግ የሚወረስ ሊሆን እንደሚችል መረጃው ይገልጻል፡፡ በእናት ወይንም በአባት አለበለዚያም ከቤተሰብ መካከል እንደ እህት ወይንም ወንድም ያሉ ሰዎች ሕመሙ ካለባቸው ወደሌላ የመተላለፉ እድል ከሀያው አንዱ ላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ ከሰው ወደሰው የመተላለፉ እድል በእድሜም ወደ 40 አመት ሲደርሱ ሊሆን ይችላል፡፡
Epilepsy የሚጥል በሽታ በየትኛውም እድሜ ሊጀምር ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን ከ20 አመት በታች እና እድሜአቸው ከ65 አመት በላይ ባሉ ሰዎች ላይ ይታያል፡፡ ወጣቶች ላይ ችግሩ የሚስተዋልበት ምክ ንያትም አንዳንድ ጊዜ በሚወለዱበት ወቅት እንደ ኢንፌክሽን ባሉ ምክን ያቶች ሲሆን በትላልቅ ሰዎች ላይ ደግሞ እንደ እስትሮክ ባሉ ህመሞች ምክንያት የሚጥል በሽታ ሊከሰት ይችላል፡፡
Epilepsy የሚጥል በሽታ ያለባቸው ብዙ ሴቶች በእርግዝናቸው ወቅት ምንም ችግር ሳይገ ጥማቸው ከአስሩ ዘጠኙ ወይንም ደግሞ (90%) የሚሆኑት ጤነኛ ልጅ እንደሚወልዱ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ህመሙ ያለባቸው ሴቶች አንዳንድ ጊዜ ወይንም በስሱ በሚባል ደረጃ ጤነኛ ልጅ የመውለድ ችግር ሊገጥማቸው የሚችል ሲሆን የዚህም ምክንያቱ እርግዝናው ከሚ ገጥመው የአፈጣጠር ችግር ወይንም በድንገት ሕመሙ በሚከሰትበት ጊዜ በሚኖረው መውደቅ ወይንም መጋጨት የተነሳ እንዲሁም ህመሙን ለመከላከል ወይንም ለሌሎች ህመሞች ሲባል በሚወሰዱ መድሀኒቶች የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡
በተለይም እናትየው እና አባትየው ሁለቱም የሚጥል በሽታ ያለባቸው ከሆነ በተለይም ህመሙ በልጅነት ጊዜ የጀመረ ከሆነ ልጅን ወልዶ የማሳደግ ኃላፊነቱን በትክክል ይወጣሉ ማለት ያስቸ ግራል። ህመሙ በልጅነት ጊዜ የጀመረ ከሆነ የተባለበት ምክንያት ልጅ ወልደው ከማሳደግ በፊት ችግሩ ከተከሰተ ልጆች የሚፈልጉዋቸውን በርካታ ነገሮች አሟልቶ ጤንነታቸውን ጠብቆ ለማሳደግ በድንገት  የሚከሰተው ህመም እውክታን እንዳይፈጥር ስለሚያሰጋ ነው፡፡ ነገር ግን ከላይ እንደተገለጸው  የሚጥል በሽታ ያለባቸው ባልና ሚስት በትክክል ሕክምናቸውን የሚወ ስዱ ከሆነ ካለምንም ችግር እስከ 90% የሚ ደርሱት ጤናማ ልጆችን ወልደው ማሳደግ ይችላሉ፡፡ በእርግዝና ወቅት የሚደርስ ድንገተኛ የህመም መከሰት የሚከተሉትን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል፡፡
የጽንሱን የልብ ምት እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል፡፡
ጽንሱ የሚያገኘውን ኦክስጂን ሊቀንስ ይችላል፡፡
ጸንሱ እንዲጎዳ ሊያደርግ ይችላል፡፡
እንግዴ ልጁ ካለጊዜው ከማህጽን እንዲላቀቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡
በሚፈጠረው ድንገተኛ መውደቅ እና በመሳሰሉት ጉዳቶች ጽንሱ ሊጎዳ ይችላል፡፡
ስለዚህም ይህንን የሚጥል በሽታን ጉዳቶች ለመከላል የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶችን በተገቢው መንገድ መጠቀም ተገቢ ይሆናል፡፡
የሚጥል በሽታን እና እርግዝናን በሚመለከት አንዳንድ መታወቅ ያለባቸው ነጥቦች አሉ፡፡ በእርግጥ ሕመሙን ሲያስቡት ወደእርግዝናው መሸጋገር ከባድ ለሚስል ይችላል፡፡ ነገር ግን መፍትሔው በተጠቃሚውም በአገልግሎት ሰጪውም እጅ ነው ይላል ማዮ ክሊኒክ ያወጣው መረጃ፡፡
Epilepsy በእርግዝና ወቅት የተለየ ትኩረትን የሚሻ ነው፡፡ ምንም እንኩዋን አብዛኞች ሕመሙ ያለባቸው ሴቶች እርግዝናቸውን በሰላም ጨርሰው ጤናማ ልጅ መውለድ የሚችሉ ቢሆንም በእርግዝው ወቅት ግን ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትል ወይንም ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው እሙን ነው፡፡
በአጠቃላይ አንዲት ሴት የሚጥል በሽታ ካለባት ከእርግዝናው በፊት ከህክምና ባለሙያ ጋር ፕሮግራም በመያዝ መመካከር፤መመርመር ይገባታል፡፡ የህክምና ባለሙያዎቹ በእርግዝና ጊዜ ሊኖረው ስለሚገባው ጥንቃቄ፤ ስለሚወሰደው መድሀኒት፤ ስለ አኑዋኑዋር ዘዴ፤ ቅርብ ካሉ ሰዎች ጋር ሊኖር ስለሚገባው መግባባት እና ምን ያህል በቅርበት ሊከታተሉአት እንደሚገባቸው የመሳ ሰሉትን መመካከር ይጠበቅባታል፡፡
በህመሙ ምክንያት የሚፈጠረው ድንገተኛ መውደቅ በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነ ምናልባትም ህመሙ በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስ እርግዝናውን ማዘግየት እና ለህመሙ የህክምና ክት ትል ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ጤናማ ምግብ መመገብ፤ በሕምና ባለሙያ የታዘዙ መድሀኒቶችን በተገቢው መውሰድ፤ በቂ እንቅልፍ መተኛት እና ሲጋራ ማጤስ..አልኮ ሆል መጠጣት..ሱስ አስያዥ እጾችን መጠቀምን ማስወገድ ጠቃሚ ነው፡፡


Read 12421 times