Print this page
Saturday, 13 March 2021 12:16

ዳሸን ባንክ በሴቶች ብቻ የሚመራ ቅርንጫፍ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ባለፉት 25 ዓመታት በስኬትና በቀዳሚነት የዘለቀው ዳሸን ባንክ የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በሴቶች ብቻ የሚመራ አዲስ ቅርንጫፍ ከፈተ። ባለፈው ሰኞ ረፋድ ላይ ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሞል ፊት ለፊት በሚገኘው ኖክ ህንፃ ላይ ተከፈተው ይሄው ቅርንጫፍ ከ10-14 ሴቶች ይመሩታል ተብሏል። በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙን ጨምሮ በርካታ የባንኩ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን የአርትስ ቴሌቪዥን ስራ አስኪጅ አርቲስት አዜብ ወርቁ በክብር እንግድነት ተገኝታ ሪቫን ቆርጣለች።
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ አስፋው “በሴቶች የሚመራ ቀርንጫፍ የከፈትነው ፋሽን ለመከተል ሳይን በባንክ ፖሊሲያችን ላይ ሴቶችን ወደ አመራር የማምጣትና የማብቃ ጉዳይ ተፅፎ የተቀረፀ በመሆኑ ያንን እውን ለማድረግ ነው” ካሉ በኋላ በባንኩ ከሚገኙ ከ10 ሺህ በላይ ሰራተኞች 29 በመቶዎቹ ሴቶች ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ከ10 በመቶው በላይ በተለያየ የአመራርነት ቦታ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ሴቶች በተሰጣቸው ተፈጥሮና የእናትነት ባህሪ ደንበኞችን በአግባቡ በማስተናገድ፣ በመንከባከብም ሆነ የቁጠባ ባህልን በማሳደግ በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል። በክብር እንግድነት ተገኘችው አርቲስት አዜብ ወርቁ በመጋበዟ የተሰማትን ደስታ ገልፃ ባንኩ ለሴቶች እየሰጠ ያለው ቦታ በማህበረሰቡ በኩል ያለውን ተገቢ ልሆነ የ”ሴቶች ኤችሉም” መንፈስ የሰበረ ነው ስትል አድናቆቷን ገልፃለች። ባንኩ 25ኛ ዓመቱን በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ ይገኛል።

Read 3004 times