Monday, 15 March 2021 00:00

“ማስተዋል” መፅሐፍ ሀሙስ መረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

      በደራሲ ፈለቀ ጌታቸው  የተጻፈውና በሀገር በቀል የስነ-ልቦና ጉዳዮች ላ የሚተኩረው “ማስተዋል” መፅሀፍ ሀሙስ መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ይመረቃል። በዕለቱ ወዳጅነህ ማህረነ (ዶ/ር)፣ የፍልስፍና ምሁሩ ዮናስ ዘውዴ፣ ተመስገን ሀይሉና ብሌን ተዋበ ሲስኩር፣ አርቲስት ፍቃ ከበደ እና አንዱአለም አባተ(የአፀደ ልጅ) ወግ የሚያቀርቡ ሲሆን ገጣሚያኑ ትዕግስት ማሞና ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙ ግጥም እንደሚቀርቡና መድረኩ በአርቲስት ካሌብ ዋለልኝ እንደሚመራ  ለማወቅ ተችሏል። መረሃ ግብሩ በሶል ኤም የሙዚቃ ባንድ ይታጀባልም ተብሏል። ደራሲው ከዚህ  ቀደም “ማስተዋል” የተሰኘ የግጥም መፅሐፍ ለንባብ ያበቃ ሲሆን “ ማስተዋል” የስነ-ልቦና መፅሐፉን ከራሱ የህይወት ልምድ  በመቀመር ሌሎች እንዲማሩበት በማሰብ ማሰናዳቱም ታውቋል። መፅሐፉ በ171 ገጽ ተቀንብቦ በ200 ብር ለገበያ ቀርቧል።

Read 9081 times