Print this page
Saturday, 20 March 2021 11:57

‹የሩዋንዳ ሰቆቃ› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(6 votes)

    በሩዋንዳ በተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ላይ የሚያተኩረውና ‹ሌፍት ቱ ቴል› የተሰኘው በእንግሊዝኛ የተጻፈ መጽሐፍ ‹የሩዋንዳ ሰቆቃ› በሚል ወደ አማርኛ ተመልሶ  ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
ደራሲዋ ኢማኩሊ፣ በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ወቅት፣ ቤተሰቦቿ ተጨፍጭፈው ሲያልቁ፣ በተአምር የተረፈች ሴት ናት፡፡ በ91 ቀናት አስጨናቂ የዘር ፍጅት ወቅት ያሳለፈችውን ሰቆቃ በመጽሐፉ  የተረከችው ኢማኩሊ፤ አሁን  ነዋሪነቷ በአሜሪካ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1994 የተጀመረው የሩዋንዳ የዘር ፍጅት፣ በ90 ቀናት ውስጥ ብቻ ወደ 900 ሺ የሚጠጉ ሰዎች ያለቁበት አሳዛኝና ሰቅጣጭ ክስተት ነበር፡፡
‹ሌፍት ቱ ቴል› የሚለውን ይሄን  መጽሐፍ ወደ አማርኛ የመለሰው  በ”አዲስ አድማስ” ጋዜጣ ላይ ለረዥም ጊዜያት የተለያዩ ጽሁፎችን፣ ወጎችንና አጫጭር ልብወለዶችን በመጻፍ የሚታወቀው ደረጀ ይመር  ነው፡፡
በ210 ገጾች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ120 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን  ሊትማን ቡክስ እንደሚያከፋፍለውም ታውቋል፡፡

Read 12532 times