Saturday, 20 March 2021 12:07

እርግዝና እና Epilepsy (ድንገት የሚጥል ሕመም)

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

   እ.ኤአ. MARCH 26 በየአመቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ የሚውለው Epilepsy የሚጥል ሕመም የ2021/ እለት የፊታችን አርብ ይውላል፡፡ ሁሉም ሰው በእለቱ የወይን ጠጅ ቀለም ያላቸውን ምልክቶች ወይንም አልባሳት እንዲጠቀም በየአመቱም ግንዛቤን የማስጨበጥ ስራዎች እንዲከ ናወኑ እንዲሁም በእለቱ ሕመሙን በሚመለከት ምን መደረግ እንደ ሚገባው የሚመ ክሩ እንደ Association of Nova Scotia (EANS) ያሉ የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ለንባብ የሚያወጧቸው መረጃዎች አሉ፡፡  
ባለፈው ሳምንት እትም የዚህን ሕመም ጥንቃቄ እና በመጠኑም ቢሆን ከእርግዝና ጋር በተገናኘ ሊሰጥ የሚገባውን ትኩረት አሰነብበናል፡፡ በዚህ እትምም እርግዝናንና Epilepsy በሚመለከት ቀሪ ነጥቦችን እነሆ ለንባብ ብለናል፡፡
Epilepsy የሚገለጽባቸው የህመም አይነቶች በwww.eplepsyscotland.org.UK እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
አእምሮን መሳት፤ ለአደጋ መጋለጥ፤
በራስ መተማመን ያለመቻል፤ ለራስ ዝቅተኛ ግምት መስጠት፤
አስቀድሞ መፈረጅ፤ በሌሎች መገለል፤
የስራ እድል ማጣት፤ የመንጃ ፈቃድ መያዝ አለመቻል፤
በሕክምና ምክንያት ለሚፈጠሩ የጎንዮሽ ጉዳቶች መጋለጥ፤
መገለል፤ ለብቻ ከቤት መውጣትን መፍራት፤
የመሳሰሉት ችግሮች በታማሚዎች ላይ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡
Epilepsy ላለባቸው ሴቶች እርግዝና ችግር አያስከትልምን? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ አባባሎች አሉ፡፡ እናትነት ከምንም በላይ የሚያስደስት የተፈጥሮ ስጦታ ነው፡፡ በእርግጥ ድንገተት የሚጥል ወይንም epilepsy ያለባቸውን ሴቶች በሚመለከት የተለያዩ የግል አመለካከቶች እና ከሰዎቸች የሚሰሙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገርግን እውነታው እንደሚከተለው ነው የሚለው Epilepsy Foundation ነው፡፡
Epilepsy ስላለብኝ ብቻ እርግዝና ከመከሰቱ በፊት ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ አይጠበቅብኝም የሚሉ ሴቶች ያጋጥማሉ፡፡
እውነታው ግን እርግዝና ከመከሰቱ በፊት ጉዞው በእቅድ የተመራ መሆን አለበት፡፡ እርግዝናው ከመጀመሩ በፊት የሚመለከታቸውን የህክምና ባለሙያዎች ማማከር ጠቃሚ ነው።
Epilepsy ካለብሽ እርግዝና ከባድ ሊሆን ወይንም መካንነት ሊያጋጥም ይችላል?
እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ጥናቶች የሚጠቁሙት ቀደም ሲል የነበረ የመካንነት ታሪክ ከሌለ ወይንም እርግዝናን የሚከለክል የተለየ ሕክምና ካልተደረገ በስተቀር Epilepsy ያለባት ሴት እንደማንኛዋም ሕመሙ እንደሌለባት ሴት ልጅ ማርገዝ ትችላለች፡፡   
የ Epilepsy መድሀኒት በእርግዝና ጊዜ መውሰድ አይቻልም የሚሉ አሉ፡፡
እውነታው ግን  እንደሐኪሞቹ እምነት እና እንደመድሀኒቱ አይነት የሚወሰን ነው፡፡ መድሀኒቱ መጠኑ ሊቀነስ ወይንም ወደ አዲስ መድሀኒት መሸጋገር ሊኖር ይችላል እንጂ በደፈናው የሚቋረጥ ነገር አይደለም፡፡
Epilepsy ካለብኝ ህመሙ ወደ ልጄም ይተላለፋል የሚል ጥርጣሬ አለ፡፡
እውነታው ግን ሁልጊዜ ያጋጥማል የሚል አይደለም፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ሕመሙ በቤተሰብ ውስጥ ይኖራል ቢባልም ነገር ግን መፈራት ያለበት አይደለም፡፡ ብዙ ህጻናት Epilepsyን ከወላጆቻቸው ሲወርሱ አይታይም፡፡ በአጠቃላይ ከ1% እስከ 5%ያህል ህጻ ናት ህመሙ ሊገጥማቸው የሚችል ሲሆን አባትየው ጭምር Epilepsy ካለበት ትንሽ  ከፍ ሊል ይችላል፡፡ ምናልባትም ልጁ Epilepsy ከያዘው ህመሙ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚችል መሆኑን መዘንጋት አይገባም፡፡  
Epilepsy በእርግዝና ወቅት በተደጋጋሚ በድንገት ሊጥል ስለሚችል አደጋው ይጨምራል የሚል እምነት ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡
እውነታው ግን አንዳንድ እርጉዝ ሴቶች በተደጋግሚ ህመሙ ቢከሰትቸውም አንዳንዶች ደግሞ አይከሰትባቸውም፡፡ በእርግጥ አደጋ መኖሩ ባይካድም በህክምና በመረዳት በቁጥጥር ስር ሊውል የሚችል መሆኑን መዘንጋት እንደማይገባ ያስረዳል፡፡ በእርግዝና ጊዜ ሕመሙ እንዲባባስ ሊያደርጉ የሚችሉ አንዳንድ እውነታዎች መኖራቸውን መጠቆም እንወዳለን ይላል የEpilepsy Foundation መረጃ፡፡
በእርግዝና ወቅት ብዙ የሳይኮሎጂ፤ ሆርሞን ለውጦች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ለውጦች ለEpilepsy ተደጋጋሚ የሆነ ድንገተኛ መከሰት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
እነዚህ ለውጦች ሰውነት ለEpilepsy የሚሰጠውን መድሀኒት ውጤታማነት ለመቀነስ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
በእርግዝና ወቅት የሚከሰተው ማስታወክ የEpilepsy መድሀኒት ከሰውነት ጋር ሳይዋሀድ ተመልሶ እንዲወጣ ሊያደርግ ይችላል፡፡
በእርግዝና ጊዜ ሰውነት ክብደት ሊጨምር ስለሚችል የመድሀኒቱ አወሳሰድም ከተከሰተው ክብደት ለውጥ ጋር እንዲጣጥም ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
እርግዝና ስሜታዊ ለውጥን ጭንቀትን እንዲሁም እንቅልፍን ማዛባት የመሳሰ ሉትን ሊያስከትል ስለሚችል በEpilepsy ምክንያት ድንገት መታመም ሊደጋገም ይችላል፡፡
በተጨማሪም አንዳንድ Epilepsy ያለባቸው ሴቶች በእርግዝና ጊዜ የደም ግፊት ሊከሰትባቸው ስለሚችል አስቀድሞውኑ መጠንቀቅን ይሻል፡፡
በ Epilepsy ምክንያት ድንገት የመውደቅ አደጋ ቢደርስብኝ እርግዝናዬ ሊጨናገፍ(ውርጃ) ይችላል የሚል ፍርሀት የሚታይባቸው አሉ፡፡
እውነታው ግን ይህን በእርግጠኝነት መደምደም ትክክል አይደለም ይላል። በእርግጥ አንዲት እርጉዝ ሴት በድንገት በሆድዋ ብትወድቅ ጽንሱን እንደሚጎዳ ወይንም ጽንሱ ካለጊዜው እንዲወለድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡ ቢሆንም ግን ብዙ ሴቶች የህክምና ክትትላቸውን በሚገባ በማድረግ ጤናማ ልጅ እንደሚወልዱ ማረ ጋገጥ ተችሎአል፡፡ ስለዚህ እርግዝናው ሲከሰት በአፋጣኝ የህክምና ባለሙያን ማማከር ጠቃሚ ነው፡፡
Epilepsy ስላለብኝ ልጄን ስወልድ የግድ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ማግኘት አለብኝ?
በEpilepsy ምክንያት በወሊድ ጊዜ የቀዶ ሕክምና ማድረግ ግድ አለመሆኑን እና እንደማንኛዋም ሕመሙ እንደሌለባት ሴት በተፈጥሮአዊ መንገድ መውለድ እንደሚቻል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የወላድዋ ሴት እና የህክምና ባለሙያዋ እምነት እንዲሁም  በተለያዩ ምክንያቶች ከሚደረግ ውሳኔ በስተቀር Epilepsy መኖሩ ለቀዶ ሕክምና አያደርስም፡፡
Epilepsy ስላለብኝ ልጅ ብወልድ ጡት ማጥባት አልችልም ብለው የሚጠራጠሩ አሉ፡፡
እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ የተለያዩ የህክምና ተቋማት ህጻናቱ ጡት መጥባት እንዳለ ባቸው ይመክራሉ፡፡ በእርግጥ ቀደምሲል የነበሩ ጥናቶች በEpilepsy ምክንያት ከሚወ ሰደው መድሀኒት ጋር ተያይዞ ወይንም በጤናው መጉዋደል ምክንያት ከሚኖ ረው ስጋት የተነሳ ህጻናቱ ጡት እንዳይጠቡ ይመክሩ ነበር፡፡ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች ግን የሚጠቁሙት ህጻናቱ እናትየው ለEpilepsy ከምትወስደው መድሀኒት በጡት በኩል ሊያገኙ የሚችሉት እጅግ በጣም ጥቂት መሆ ኑን እና በጡት ወተቱ ምክንያት የሚያገኙት ጥቅም ስለሚበልጥ የእናታቸውን ጡት እንዲጠቡ ይመክራሉ። በእርግጥ አንዳንድ መድሀኒቶች ለህጻናቱ አደገኛ ይሆናሉ ቢባል እንኩዋን የህክምና ባለሙያዎቹ ሊያስተካክሉት የሚችሉት በመሆኑ ውሳኔውን ለእነሱ መተው ይገባል፡፡
  MARCH 26/ አለምአቀፍ የEpilepsy (ድንገት የሚጥል ሕመም) ቀን፡፡

Read 11575 times