Saturday, 03 April 2021 18:38

በ“ክብር ዘበኛ የስልጣኔ ፈር የለውጥ ፋና ወጊ” ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በብራና ወርሀዊ የመፅሀፍት ውይይት፣ በጃፋር መፅሀፍት መደብርና በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃህፍት ኤጀንሲ ትብብር “ክብር ዘበኛ የስልጣኔ ፈር የለውጥ ፋና ወጊ” በተሰኘው በጋዜጠኛና አርታኢ አየለ እሸቱ መፅሀፍ ላይ ነገ መጋቢት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ- መዛግብትና ቤተ መፅሀፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡
ለዕለቱ ውይይት የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የታሪክ ሙሁሩ ረ/ፕ አበባው አያሌው ሲሆኑ ፍላጎት ያለው በውይይቱ እንዲሳተፍ አዘጋጁ ብራና ወርሃዊ የመፅሀፍት ውይይት ጋብዟል፡፡

Read 18610 times