Saturday, 10 April 2021 13:41

COVID-19 - የእናቶች እና ጨቅላዎች ሞት

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)


          በኢትዮጵያ የእናቶችንና የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውጤት መታየ ቱን የዘገበው 12 March 2019 WHO ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን በተለይም ከ COVID-19 ጋር በተያያዘ ያለው የሞት መጠን ምን ይመስላል የሚለውን ከGynecology & Obstetrics 24 July 2020 ያወጣውን ሪፖርት እናስነብባችሁ፡፡  
በአለም ላይ የCOVID-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ሪፖርት የተደረገው 160 እናቶች መሞታቸው ነው፡፡ እነዚህ ሟቾች አብዛኛዎቹ በመካከለኛ ገቢ ከሚተዳደሩ አገራት ሲሆኑ እነዚህም የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የተለያዩ ችግሮች ካሉባቸው አገራት ናቸው፡፡
ከአሁን ቀደም በአንዳንድ ጥናቶች እንደተጠቆመው በእርግዝና ላይ ያሉ እናቶች እርግዝና ላይ ካልሆኑት ይልቅ በከፋ ሁኔታ በኮሮና ቫይረስ ይያዛሉ ወይንስ አይያዙም የሚለውን ለመለየት አስቸጋሪ የነበረና ሁኔታዎች ሲታዩም እርጉዝ ሴቶች በተለየ መልኩ ለዚህ ቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ የሚል ምንም ማሳያ እንዳልነበረ ተደጋግሞ ተጠቅሶአል፡፡ በቅርብ ጊዜ ከአሜሪካ እና ስዊድን የወጡ ጥናቶች ግን በእርግዝና ላይ ያሉ እና ከወሊድ በሁዋላ ሴቶች ከሌሎች ይልቅ ከፍ ባለ ደረጃ በቫይረሱ ምክንያት ለሚከሰተው ኢንፌክሽን ሊጋለጡ እንደሚችሉ ጠቁሞአል፡፡
ቁጥራቸው ወደ 8207 የሚሆኑ ሴቶች ላይ በተደረገው ፍተሻ (CDC) የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ አካል አንዳረጋገጠው በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ቫይረሱ በሚይዛቸው ጊዜ እርጉዝ ካልሆኑት እና ቫይረሱ ከያዛ ቸው ሴቶች በበለጠ በጽኑ ሕሙማን ክፍል መተኛት ግድ እንደሚሆንባቸው እና ኦክስጂን በአየር መሳቢያ እንደሚሰጣቸው ተረጋግጦአል፡፡ በእርግጥ ለሞት የመጋለጥን ነገር በሚመለከት አሁንም የከፋ ነው የሚያሰኝ ሪፖርት አልተገኘም፡፡
የኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽንንና የእናቶችን ሞት በሚመለከት እ.ኤ.አ December 2019 until July 1,2020 በተደረገው ፍተሻ ወደ ስድስት የሚሆኑ ሀገራት በCOVID-19 ምክንያት የእናቶች ሞት መከሰቱን የሚያሳዩ ሪፖርቶች በ July 1, 2020 አቅርበዋል፡፡ እነዚህ ሀገራትም ሶስቱ ከፍተኛ ገቢ ያላቸው (ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ) ሲሆኑ ሶስቱ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ደግሞ (ብራዚል፤ ኢራን እና ሜክሲኮ) ናቸው፡፡  በጥቅሉ ሪፖርት የተደረገው የእናቶች ሞት 160 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 22/የሚሆነው የእናቶች ሞት በከፍተኛ ገቢ ባለቸው ሀገራት ሲሆን የቀሩት 138 የሚሆኑት ሞቶች ደግሞ በመካከለኛ ገቢ ባለቸው አገራት ውስጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ 124 የሚሆኑት በብራዚል ስለሆነ ይህም 77.5% የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል፡፡
ከCOVID-19 ጋር በተያያዘ በአለም ላይ የሚደርሰው የእናቶች ሞት ምን ያህል እንደሆነ ለመረዳት የተጠቀሰው መረጃ በቂ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ካሉት ሀገራት የተገኘ መረጃ ስለሌለ ችግሩ የተጠቀሰው ብቻ ነው ብሎ መደምደም አይቻልም፡፡
የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በመደረግ ላይ ያለው የአለም አቀፍ ጥረት ከጥቂት አመታት ወዲህ እየተተገበረ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ2030 ቀጣይነት ያለው የልማት ግብ ውስጥ በመካተቱ በተለይም በመካከለኛ እና በአነስተኛ ደረጃ በሚኖሩ ሀገራት ውጤታማ እንደሚሆን እምነት አለ፡፡ቢሆንም ግን በCOVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት እናቶች ወደጤና ተቋም እንዳይሄዱ ምክንያት እንዳይሆንና በዚህም ሞትን እንዳያስከትል ስጋት አለ፡፡  
የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ በወሲባዊ እና የስነተዋልዶ ጤና ላይ ያደረሰው ተጽእኖ ይኖር ይሆን የሚለውን በኢትዮጵያ እውነታውን ለመመልከት የሞከሩ ባለሙያዎች እንደሚከተለው አስነብ በዋል ፡፡ ባለሙያዎቹን ማግኘት ለሚፈልግ አድራሻቸው Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ; Phone: +1-267 359 6135 Introduction ነው፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ሲመዘን ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በወሲባዊና ስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ከፍያለ ስራ መሰራቱንና በተለይም የእናቶችን ሞት መቀነስ እና ደህንነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ ሰፋ ያለ ስራ መሰራቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ያደረገችው ጥረት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ሁሉም እናቶችን የሚመለከቱ ማለ ትም የእርግዝና ክትትልን የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን እና ከጽንስ ማቋረጥ ጋር በተያያዘ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በነጻ ለታማሚዎች እንዲደርስ ስርአት ተዘርግቶ ተግባራዊ በመ ደረግ ላይ ያለ ነው፡፡ በዚህም ተጠቃሚዎች ወደጤና ተቋም እና የሰለጠነ ባለሙያ እንዲቀርቡ የሚያበረታታ ሆኖአል፡፡
በ2019/ 7‚091‚000 የሚሆኑ ሴቶች ዘመናዊ ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ በመውሰዳቸው ወደ 2‚755‚000 የሚሆኑ ያልታቀዱ እርግዝናዎችን 607,000 የሚሆኑ ደህንነታቸው
ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥን እና 7400 የሚሆኑ የእናቶች ሞትን ለመቀነስ አስችሎአል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በተለይም የንቃተ ሕሊና መጨመር እንዲኖር የሚያስችል ትምህርት በጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች እና በሚመለከታቸው ለህብረተሰቡ በመሰጠቱ ነው፡፡
መረጃው እንደሚጠቁመው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የእናቶችንና የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመ ቀነስና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የሚደረገውን ጥረት እንዳያስተጉዋጉል ይፈራል፡፡ አንዳንድ መረጃዎች የህክምና ባለሙያዎችን ምንጭ አድርገው እንደሚጠቁሙት እርጉዝ የሆኑ ሴቶች ለመውለድ ወደጤና ጣቢያ ለመምጣት የሚያደርጉትን ጉዞ በመፍራት በቤታቸው መውለድን የሚመርጡ ብዙ ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያን በጊዜው ለማቅ ረብ ከመጉዋጉዋዣ ጋር በተያያዘ ችግሮች እንደሚስተዋሉና ህብረተሰቡም አገልግሎቱን ለማግ ኘት መሄድን የሚያቋርጥበት ሁኔታ ተስተውሎአል፡፡ በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ በተጨማሪ እንደ ብጫ ወባ ያሉ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችም ችግር ማስከተላቸው አልቀረም፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ጤንነት ከኮሮና ቫይረስ አንጻር ሲታይ የእናቶች ንና የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ የሚሰራውን እና ውጤታማ የሆነውን እንቅስቃሴ እንዳ ያዳ ናቅፍ ትኩረትን የሚሻ መሆኑን ጥናት አቅራቢዎች ይገልጻሉ። ከዚህ በተጨማሪም እር ጉዝ ሴቶች እራሳቸውን ከህመሙ የሚከላከሉበትንና ወደጤና ተቋም እና ወደ ሰለጠነ ባለ ሙያ መቅረብን እንዳይተዉ በማድረግ ረገድ ህብረተሰቡ ኃላፊነት የተጣለበት መሆኑን መዘንጋት አይገባም፡፡
ይህ ጽሁፍ እስከተጠናቀረበት ድረስ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3000/የደረሰ ሲሆን በ24 ሰአት ውስጥ 37 ሰዎች እንደሞቱ ተመዝግቦአል፡፡ በ24 ሰአት ውስጥ 2‚138 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን እና ይህም በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር ወደ 217‚327 ያሳድገዋል፡፡ 51‚303 የሚሆኑ ሰዎች በመላ አገሪቱ በሕክምና ላይ የሚገኙ ሴሆን ወደ 862 የሚሆኑት በከፍተኛ ደረጃ ክትትል የሚደረ ግላቸው  ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከደቡብ አፍሪካ፤ ሞሮኮ እና ቱኒዝያ ቀጥላ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች በብዛት ያሉባት ሀገር ለመባልም በቅታለች፡፡   
ከላይ ከተጠቀሰው እውነታ ወጣ በማለት በኢትዮጵያ ያለውን የእናቶች ሞት መቀነስ እንዲሁም ጽንስን ማቋረጥ ወይንም ጽንሱ ሕይወት የሌለው ሆኖ መጨናገፍን መቀነስን በአዲስ አበባ የሚገኘው የአለም የጤና ድርጅት 12 March 2019 WHO እንደሚከተለው ዘግቦታል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጤና እንክብካቤ የጥራት ስትራቴጂ ከ2016-2020 ባለው ጊዜ ውስጥ የእናቶች፤ጨቅላዎች እና ህጻናትን ጤና በማስቀደም በእቅድ ለተያዘው የእናቶችና ህጻናት ሞት መቀነስ እንዲያገለግል ተነድፎአል፡፡ በዚህም እቅድ መሰረት በኢትዮጵያ በ2020 የእናቶች ሞት መጠን በህይወት ከሚወለዱ ከ1000/ ከ412 ወደ 199 ለመቀነስ የጨቅላ ህጻናትን ሞት ከ1000/ በሕ ይወት ከሚወለዱ ህጻናት ከ28 ወደ 10 ለመቀነስ እንዲሁም ሕይወት አጥተው ከሚወለዱት ከ1000 መካከል ከ18 ወደ 10 ዝቅ እንዲል ማድረግ ነው፡፡   
ኢትዮጵያ በአገሪቱ በመላው አካባቢ ያሉ ሴቶች በእርግዝና ጊዜ እንዲሁም በወሊድ እና የተ ወለዱ ጨቅላዎችን አገልግሎት በመስጠቱ እና (Quality of Care Network) የእንክብካቤ ጥራት መረብን በመጠቀም ረገድ እንዲሁም ከወሊድ በሁዋላ በሚደ ረገው ክትትል የእናቶችን እና የጨቅላዎቻቸውን ደህንነትን የሚያረጋግጥ ተደራሽነት ባለው እና ሁለገብ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠቱ ረገድ ከፍተኛ ደረጃ ከሚሰጣቸው 10/ አገራት መካከል ፊት ቀደም መሆኑዋ በአዲስ አበባ የአለም የጤና ድርጅት አረጋ ግጦአል፡፡
እ.ኤ.አ በ2017 ከአለም የጤና ድርጅት ዩኒሴፍ እና ዩኤንኤፍፒኤ ጋር እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የተዘረጋው የእንክክካቤ ጥራት መረብ በአገራቱ በብሄራዊ ደረጃ ለሚ ተገበሩት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጠቃሚ መሆኑ እሙን ነው፡፡ በዚህ ፕሮ ግራም የታቀፉ ሌሎች ሀገራትም በ2022 /የእናቶች ፤የጨቅላ ህጻናት እና የጽንስ ማቋረጥ ወይንም ውርጃ ለመቀነስ እና የታማሚዎችን እንክብካቤ ለማሻሻል እንደሚረዳ ታምኖ በታል፡፡

Read 10456 times Last modified on Saturday, 10 April 2021 14:24