Print this page
Saturday, 17 April 2021 00:00

የአንጋፋው ጋዜጠኛ አባተ መንደፍሮ ሀይሉ “ታልከል” መፅሀፍ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የእውቁና አንጋፋው ጋዜጠኛ አባተ መንደፍሮ ሀይሉ “ታልከል” መፅሐፍ  ባለፈው ረቡዕ በጊዮን ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ ውስጥ ተመረቀ፡፡ በምርቃት ስነ-ሥርዓቱ ላይ ግጥሞች፣ ከመፅሐፉ ላይ የተቀነጨቡ ታሪኮችና ሌሎችም መሰናዶዎች የቀረቡ ሲሆን አንጋፋውን ጋዜጠኛ አባተ ማንደፍሮን ከልጅነት እስከ እውቀት የሚያውቁትና አብረውት የሰሩ ጓደኞቹ ስለ እርሱ ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ መፅሐፉ 11 አጫጭር ልቦለዶችን የያዘ ሲሆን 132 ገፅፆች ተቀንብቦ በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ደራሲና ጋዜጠኛ አባተ ማንደፍሮ ሀጉን በውትድርና ያገለገለ ሲሆን የወሎ ላሊበላ ኪነት የመድረክ አስተዋዋቂ፣  በመፅሄቶችና ጋዜጦች ላይ በኮሪፖርተርነት እስከ ዋና አዘጋጅነትም ሰርቷል፡፡
አቢሲኒያ ኢንተርቴይመንት የተሰኘ የራሱን የሬዲዮ ፕሮግራም በ96.3 F.M እና ዛሚ 90.7 ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡ በዚህ ፕሮግራሙ የቀጥታ የሬዲዮ የድምፃዊያን ውድድር በማካሄድ ለአሸናፊዎቹም  ግጥምና ዜማ በመስጠት ነጠላ ዜማ እንዲያወጡ እስከ መድረስ ለኪነ-ጥበቡና ለጥበበኞቹ ታላቅ ውለታ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በJTV ኢትዮጵያም በስራ አስኪያጅነት አገልግሏል፡፡
አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ አባተ ማንደፍሮ ከህመሙ ጋር እየታገለ ቢሆንም “ታልከል” የተሰኘውን መጽሐፉን ለንባብ ያበቃ ሲሆን ከዚህ ቀደም “የደም ምድር” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 18134 times