Saturday, 24 April 2021 12:28

በግንባታ ላይ የነበረ ህንጻ ተደርምሶ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

Written by  መታሰቢያ ሳሣዬ
Rate this item
(1 Vote)

  በአዲስ አበባ ከተማ ካዛንቺስ ሀናን ዳቦ እየተባለ  በሚጠራው አካባቢ፣ በግንባታ ላይ የነበረ ጅምር ህንፃ ትላንት ተደርምሶ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
ከ40 በላይ ሰራተኞች በህንጻ ግንባታው ላይ ተሰማርተው  እየሰሩ በነበረበት ወቅት መንስኤው እስከ አሁን  በግልፅ ባልታወቀ ሁኔታ ግንባታው በመደርመሱ ሳቢያ በስራ ላይ ከነበሩት  መካከል ሶስቱ ህይወታቸው ወዲያውኑ ማለፉ ታውቋል፡፡
በግንባታው ናዳ ሳቢያ የተቀበሩ ሰዎችን  ለማውጣት ርብርብ  እየተደረገ ሲሆን የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም  ሊጨምር እንደሚችልም ምንጮች ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በተደረመሰው ግንባታ ስር የሚገኙ ሰዎችን ለማውጣት የሚያደርጉት ጥረት እንደቀጠለ መሆኑ ተነግሯል፡፡

Read 8127 times