Saturday, 24 April 2021 13:16

ሕጻናት እና COVID-19፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  ይህ ጽሁፍ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ COVID-19 በአለም ላይ ስጋት ሆኖ ቀጥሎአል፡፡ በእርግጥ ክትባት ተገኝቶለታል ቢባልም እንኩዋን በመላው የአለም ህዝብ ምን ያል ወይንም ሙሉ በሙሉ ተቀባይትን አግኝቶአል ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ እንደሚታየው ከሆነ በአለም ላይ ፈቃደኛ የሆነ ሲከተብ ፈቃደኛ ያልሆነ ግን የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት እና ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት አለው በማለት አልከተብም የሚል መልስ ሰዎች ታይተዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ ፈቃደኛ ሆነው ክትባቱን የወሰዱ አስከፊና ገዳይ የሆነው ኮሮና ቫይረስ አይይዛቸውም ማለት ሳይሆን ቢይዛቸው እንኩን ለስቃይ ሳይዳረጉ ህመሙን እንደሚያሳልፉ ባለሙያዎች ያረጋግ ጣሉ፡፡  
ይህ ጽሁፍ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ባለው መረጃ መሰረት በእስራኤል በርካታ ህዝብ ክትባቱን በመውሰዱ ህብረተሰቡ ከአመት በላይ ከፊታቸው ያላወለቁትን Face Mask የአፍና አፍ ንጫ መሸፈኛ አውልቀው በሰላም ለመገናኘት ለመንቀሳቀስ በቅተዋል፡፡ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም ከሺዎች ወደ መቶዎች ዝቅ ማለቱ ተነግሮአል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በብራዚል በቫይ ረሱ ምክን ያት ያለው እልቂት በአንድ ቀን እስከ 4000/ በመድረሱ እየከፋ መሆኑ በአ ለም የመገናኛ ብዙሀን እየተነገረ ነው፡፡ በአለም ላይ በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከሶስተ ሚሊዮን የዘለለ ሲሆን በኢት ዮጵያም የሟቾች ቁጥር ከሶስት ሺህ ሶስት መቶ አልፎአል፡:፡
በዚህ እትም አንድ ልናውቅ የሚገባንን ነገር እናነባለን፡፡ ለመሆኑ ህጻናት፤ ታዳጊዎች የኮሮና ቫይረስ ይይዛቸዋልን የሚለውን መረጃዎች CDC (የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማእከል) እንደሚከተለው ያካፍለናል፡፡
እስከአሁን በታየው እውነታ ምንም እንኩዋን በ COVID-19  የተያዙ ህጻናት ቁጥር ከአዋቂ ዎች ጋር ሲነጻጸር ብዛት አለው ተብሎ ተጠቃሽ ባይሆንም ነገር ግን በቫይረሱ ሊያዙ እንደ ሚችሉ ተረጋግጦአል፡፡
ህጻናት በCOVID-19  ምክንያት ለህመም ይዳረጋሉ፡፡
ህጻናት COVID-19 ከያዛቸው ለሌሎች ሰዎችም ሊያስተላልፉት ይችላሉ፡፡
ህጻናት በCOVID-19 መያዛቸውን የሚያሳይ ምንም ምልክት ባይኖርባቸውም ቫይረሱን ግን ለሌሎች ያስተላልፋሉ፡፡
አብዛኞቹ ልጆች የኮሮና ቫይረስ ሲይዛቸው ሊኖራቸው የሚችለው ምልክት በጣም ስስ የሆነ ወይንም ብዙ የሚታይ ላይሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ግን በከፋ ሁኔታ የሚታመሙበት እና ወደሆስፒታል እንዲገቡ የሚገደዱበት፤ በጽኑ ሕሙማን ክፍል ክትትል እንዲደረግላቸው የሚያስፈልግበት፤ የመተንፈሻ መሳሪያ እርዳታ የሚያስፈልግበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ህጻናቱ ሊሞቱ ይችላሉ፡፡
በእድሜአቸው ከአንድ አመት በታች የሆኑ እና ሌሎችም ህጻናት በአንዳንድ ምክንያቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለህመም ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ በተለይ ግን በእድሜአቸው ከአንድ አመት በታች የሆኑት ህጻናት በቫይረሱ ምክንያት ለከፋ ህመም ይዳረጋሉ፡፡ እድሜን መጥቀስ ሳያስፈ ልግ ሁሉም በየትኛውም ደረጃ ያሉ ህጻናት ለቫይረሱ ሊጋለጡ የሚችሉባቸው ተጠቃሽ ከሆኑ ህመሞች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
አስም ወይንም አስከፊ የሆነ የመተንፈሻ አካል ሕመም፤ የስኩዋር ሕመም፤
በትውልድ የሚተላለፍ ወይም የነርቭ የመሳሰሉት ሕመሞች፤ ከልክ በላይ ውፍረት፤
ሲወለዱ ጀምሮ ያለ የልብ ሕመም፤ የሰውነት ሕመምን የመቋቋም አቅም ማነስ
በህክምና እርዳታ ምክንያት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግለትና በቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚኖር፤ ሙሉ አካሉ በየቀኑ በሚሰጠው ድጋፍ ጥገኛ የሆነ ህጻን….ወዘተ
ከላይ የተዘረዘሩት ሕመሞች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ምክንያቶች ህጻናቱን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለከፋ ሕመም እንዲዳረጉ ሊያደርጋቸው ይችላል CDC እንደሚለው፡፡
አንድ ህጻን ከላይ የተጠቀሱት የጤና ችግሮች የሚመለከቱት ከሆነ እና ባልታሰበ ሁኔታ ህመሙ የሚገጥመው ከሆነ ከህጻናት ሐኪም ጋር መነጋገር እንደሚገባ ሁሉም ወላጅ ወይንም አሳዳጊ ማወቅ ይገባዋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ለልጆችም ለአዋቂዎችም ተመሳሳይ ሲሆኑ በተጨማሪም እንደጉንፋን፤ የአንዳንድ ነገሮች አለመስማማት (allergies) የጉሮሮ ሕመም ከመሳሰሉት ጋር አንድ አይነት ሊሆን ይችላል፡፡ ህጻናት በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ አብዛኛውን ጊዜ የከፋ ሳልና ትኩሳት ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከሚከተሉት የህመም ምልክቶች ውስጥ የተወሰኑት ሊታይባቸው ይችላል፡፡
ትኩሳት ወይንም ጭንቀት፤ የጉንፋን ተመሳሳይ ሳል፤ ከአፍንጫ በተከታታይ ፈሳሽ መውረድ፤
የአየር ቧንቧ ሕመም፤ የአየር እጥረት ወይንም የትንፋሽ መቆራረጥ፤
ተቅማጥ፤ ማስመለስ፤ የሆድ ሕመም፤ ድካም፤ ራስ ምታት፤
የጡንቻ ወይንም የሰውነት ህመም ወይንም ስቃይ፤
የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣በቂ ምግብ አለመውሰድ፤
የመሳሰሉት ከአንድ አመት በታች ባሉ ህጻናት ላይ የሚታይ ከሆነ አፋጣኝ የሆነ እርምጃ እና ክትትል ለማድረግ ይበልጡኑ የሚከተሉት ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል፡፡
ትኩሳት 38° ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ከፍ ካለ፤
የጉሮሮ ወይንም የመተንፈሻ አካል ሕመም ከፍ ካለ
ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሳልና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመ፤ ወይንም ልጁ (chronic allergic) የሆነ እንደ አስም ያለ አስቸጋሪ ወይንም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከታመመ፤
ጽኑ የሆነ ራስምታት ከትኩሳት ጋራ የሚታይበት ከሆነ እና ሌሎቹም እንደ ተቅማጥ ፤ማስታ ወክ ወይንም የሆድ ሕመም የመሳሰሉት በከፋ ሁኔታ የሚስተዋልበት ከሆነ ህጻኑን  በአፋጣኝ  ወደሕክምና ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
Global health በተባለው ድረገጽ የኮሮና ቫይረስ በቀጥታም እንኩዋን ባይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ በእናቶችና ህጻናት ላይ በተለይም በአነስተኛና በመካከለኛ ገቢ በሚተዳደሩ ሀገራት ሞት ሊያስከትል እንደሚችል ጠቅሶአል፡፡ የእናቶች፤አዲስ የተወለዱ ጨቅላዎች እና ህጻናት ተገቢውን የህክምና አገልግሎት የማያገኙ ከሆነ የሞት መጠናቸው ሊጨምር ይችላል፡፡  
በየአመቱ በአለማችን ከ2.6 ሚሊዮን በላይ ውርጃ ወይንም ጽንስ የማቋረጥ አጋጣሚ ይኖራል፡፡
በየአመቱ ወደ 2.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ጨቅላዎች ሕይወት ያልፋል፡፡
2.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ከጨቅላ እድሜ በሁዋላ ምናልባትም እስከ አምስት መት ድረስ ያሉ ህጻናት ሊሞቱ ይችላሉ፡፡
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የእናቶችና ህጻናት ሞት በአንዳንድ አካባቢዎች የቀነሰ ቢሆንም የጽንስ መቋረጥ ግን አሁንም ከፍ እንዳለ ምናልባትም እ.ኤአ. በ2030 ከሚጠበቀው ከ1000 በህይወት የሚወለዱ ወደ 12 ማድረስን ከባድ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ስለዚህ አብዛኞቹ የጽንስ መቋረጦች በተሟላ እና ጥራት ባለው የህክምና አገልግሎት እገዛ ሊሻሻሉ ይገባል፡፡
ወደ CDC ስንመለስ በተለይም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ልጆችን ላለማጣት የተወሰኑ ምክሮችን እንደሚከተለው አካፍሎአል፡፡ ልጅዎ የኮሮና ቫይረስ የመያዝ ምልክት ካሳየ….
ልጁን ከቤት እንዳይወጣ መንከባከብ፤
የህክምና ባለሙያ ሊያገኘው ይገባል አይገባም የሚለውን መወሰን፤ቫይረሱ ይዞት ይሁን ወይንም አይሁን ለማወቅ ምርመራ ማድረግ፤
ልጅን በማስታመም ወቅት እራስን በቫይረሱ እንዳይያዙ መከላከል፤
ልጅዎ ሕመም እንደተሰማውና በቫይረሱ መያዙን የሚያሳይ መረጃ ካለዎት ማሳወቅ፤
የመሳሰሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ ከሁሉም ወላጅ እንዲሁም ተንከባካቢዎች ይጠበቃል፡፡


Read 10488 times