Print this page
Saturday, 01 May 2021 12:16

ኢህአፓ ከ45 ዓመት በፊት በደርግ የተገደሉ አባላትን ዛሬ ይዘክራል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

      የዛሬ 45 ዓመት የሰራተኞች ቀንን በመስቀል አደባባይ እያከበሩ በነበረበት ወቅት “አመፅ አካሂዳችኋል” በሚል የተገደሉ የኢህአፓ አባላትን በዛሬው እለት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚዘክር ፓርቲው አስታውቋል፡፡
በ1968 ዓ.ም የሰራተኞች ዓመታዊ በአል በሚከበርበት ወቅት የሰራተኛ ማህበሩ አባልና የኢህአፓ አባላት የሆኑ በርካታ ሠራተኞች በአደባባይ ላይ የተገደሉበትን ቀን ነው ኢህአፓ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚዘክረው  ብለዋል- የፓርቲው ተ/ም ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን ተሰማ፡፡
አዲስ አበባ በሚገኘው የኢህአፓ ፅ/ቤት በሚከናወነው የዝክር ስነ-ስርዓት የሚታደሙበት ላይ የኢህአፓ የቀድሞ ታጋዮች፣ የሠራተኛ ማህበር አባላት፣በወቅቱ ህዝባዊ ጥያቄ ሲያነሱ የነበሩ ሁሉ የሚገኙበት ይሆናል ተብሏል፡፡
በእለቱም በአደባባይ የህዝብ ጥያቄን በማንሳታቸው ግድያ የተፈፀመባቸውን አባላት የሚዘክሩ የተለያዩ ዝግጅቶች ይኖራሉ ያሉት አቶ ሰለሞን በቋሚነት በሚዘክሩበት ሁኔታ ላይም ምክክር ያደርጋል ብለዋል፡፡
በዛሬው ዕለት (ሚያዚያ 23)  ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ በፓርቲው ጽ/ቤት በሚካሄደው ፕሮግራም ላይ ማንኛውም ፍላጎቱ ያለው ግለሰብ መታደም ይችላል ብሏል ኢህአፓ፡፡

Read 11770 times