INS የተሰኘ የሜካፕ ት/ቤት በ3 ዙር ያሰለጠናቸውንና በአድቫንስድ ሜካፕ ኮርስ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 55 ያህል ተማሪዎችን ባለፈው ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በጎልፍ ክለብ አስመረቀ።
ሰልጣኞቹም ለ1 ወር ያህል በፊት ማስዋብ ስራ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ወስደው መመረቃቸውም ታውቋል። ት/ቤቱ በቅርቡ የተከፈተ ሲሆን፣ በተለይም ለሰርግ፣ ለምርቃትና ለልዩ ልዩ ዝግጅቶች መዋብ የሚፈልጉ በርካቶች ያጡትን የባለሙያ እጥረት በመቅረፍና በዘልማድ የሚሰራውን የፊት ማስዋብ ስራ ሙያተኞች እንዲሰሩት በማድረግ የዘርፉ ክፍተት እንደሚሞላ የ INS ሜካፕ ት/ቤት መስራችና ፕሬዚዳንት ወንጌላዊት ጎሌ ተናግረዋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ተወካዮች፣ የኔክስት ፋሽን ዲዛይን ት/ቤት መስራች ሳራ መሀመድ አርቲስት ቤቲጂና ሌሎችም እንግዶች ታድመዋል።