Saturday, 01 May 2021 13:09

“የእግዜር ድርሰት” በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


          “አክሳሳፎስ” በተሰኘው አነጋጋሪ መፅሐፉ የስነ-ፅሁፍን ዓለም የተቀላቀለውና ስድስት ያህል መፅሐፍትን ለንባብ ያበቃው የደራሲ ይባቤ አዳነ “የእግዜር ድርሰት” መፅሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ። የደራሲው አራተኛ ስራ የሆነው ይሄው መፅሐፍ በዋናነት በመንፈሳዊ ትበባት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የፈጣሪን ስራ እየጠየቀ፣ እየሞገተ፣ እያደነቀና ከሰው ልጅ የጤና፣ የክብርና ልዩ ልዩ መንፈሳዊና ዓለማዊ ፍላጎቶች አንፃር እንደሚፈተሽ ደራሲ ይባቤ  አዳነ ገልጿል፡፡
በ196 ገፅ ተቀንብቦ በ160 ብር ለገበያ የቀረበው መፅሐፍ በሰገነት አሳታሚ ድርጅት በዋናነት እየተከፋፈለ ሲሆን በሁሉም መፅሐፍት መደብርና በአዟሪዎች እጅ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “አክሳሳፎስ”፣ “የከተማው አህያ”፣ “ስልጡን ድንቁርና”፣ ሰባት ቁጥርና ህይወት ቁጥር 1 እና 2” የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 11232 times