በ”UN WOMAN” እና በ”ሎሚ ሚዲያ” ፕሮዲዩስ የተደረገው፣ በጥረታቸው ከፍ ብለው የታዩ ሴቶችን የሚያወድሰውና በሀገር ፍቅር፣ ሰላም እና አንድነት መጠንከር ላይ የሴቶች ሚና የላቀ መሆኑን የሚያወሳው “የሀገር ካስማ” የሙዚቃ ቪዲዮ ትናንትና ሚያዚያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል ተመረቀ።
ይህ ሙዚቃ በአንጋፋና ወጣት ድምፃዊያን የተዜመ ሲሆን ኩኩ ሰብስቤ፣ ፍቅር አዲስ ነቃጥበብ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሳያት ደምሴ፣ ራሄል ጌቱ፣ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ)፣ ጌታቸው ኃ/ማርያም፣ አስገኘው አሽኮ (አስጌ ደንደሾ) እና ኤፍሬም አስራት እንደሚገኙበት ታውቋል። በዚህ የሙዚቃ ቪዲዮ ምርቃ ላይ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርገው ያስጠሩ ሴቶች ጀግኖች፣ ታላላቅ አርቲስቶች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ድምጻዊያኑና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መታደማቸውም ታውቋል።
Saturday, 08 May 2021 12:39
ሀገር ካስማ” የሙዚቃ ቪዲዮ ትላንት ተመረቀ
Written by ናፍቆት ዩሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና