Saturday, 08 May 2021 12:51

ሊሞቱ የነበሩ እናቶች ከሞት መትረፍ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

   ሊሞቱ የነበሩ እናቶች ከሞት መትረፍ ሲባል አንዲት ሴት ከእርግዝና ጋር በተያያዘ፤ ልጅ በመውለድ ጊዜ ወይንም የእርግዝና ጊዜው 42 ቀን ከሆነ በሁዋላ በሚከሰት የእርግዝና መቋረጥ ምክንያት በሚከሰቱ የተለያዩ ውስብስብ የጤና ችግሮች የተነሳ ልትሞት ደርሳ ነገር ግን ስትድን ማለት ነው፡፡ ይህንን የአለም የጤና ድርጅት በተለያዩ ጊዜያት በህክምናው ዘርፍ ሊደረግ የሚገ ባውን መመሪያ በማዘጋጀት የተሸለ እና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በየሀገራቱ አሰራጭቶአል ይላል Health Promot Perspect (Oct-2019)፡፡   
አለም እስካለንበት ጊዜ ድረስ መጨነቋን የማታቆምበት የነበረና የአለ እንዲሁም ወደፊት በሚሆ ነው ነገር ትግል የሚደረግበት ነገር ቢኖር የእናቶችን ሞት ከነበረበት መቀነስ ነው፡፡ አለምአቀፉ የልማት ግብ የእናቶችን ሞት በመቀነስ ረገድ በተለያየ መስፈርት የሚጠብቀው ነገር ቢኖርም ሀገራት ግን እስከአሁን ድረስ ያልቋጩት አጀንዳ እና የአለማችን ዋነኛ አስጨናቂ ጉዳይ ከሚ ባሉት የጤና ችግሮች ውስጥ መድበውታል፡፡ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ባሳለ ፍናቸው ጊዜአት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ቢደረጉም አሁንም ድረስ የውይይት አጀንዳ ሆኖ ይገኛል፡፡ የእናቶች ሞት ቀጣይነት ባለው የልማት ግብ አጀንዳ ውስጥም ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ የሚ ጠይቅ እና ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፡፡  
በአለም የጤና ድርጅት (WHO), እምነት ማንኛዋም በእርግዝና ላይ ያለች ሴት እና ጨቅላዋ ጥራት ያለው የህክምናን አገልግሎት በእርግዝናዋ ሙሉ ወቅት፤ በወሊድ ወቅት እና ከወሊድ በሁዋላ ማግኘት አለባት፡፡ ምንም እንኩዋን በአለም አቀፍ ደረጃ የእናቶች ሞት እ.ኤ.አ በ1990 ከነበረበት ወደ 45% ዝቅ ብሎ የተመዘገበ ቢሆንም በየቀኑ 800/እናቶች ከመውለዳቸው በፊት፤በወሊድ ጊዜና ከወለዱ በሁዋላ መሞታቸው አልቀረም Health Promot Perspect እንደሚ ገልጸው፡፡
መረጃው በመቀጠልም የአለም የጤና ድርጅት እ.ኤ.አ በ2004 ያወጣው መመሪያ የእናቶችን የእርግዝና ሕይወት ለመጠበቅ እንዲቻል የአናቶችን ሞት ቁጥር እና የገጠማቸውን ውስብስብ የሆነ የጤና ችግር ከመፈተሸ እና ከመግለጽ ባሻገር እነዚህ እናቶች መቼ ይህ ችግር ገጠማ ቸው፤ ለምን ችግሩ ገጠማቸው እና እንዴት ከችግሩ ሊላቀቁ ይችላሉ የሚለውን በጥልቀት በመፈተሸ ስራ መስራት ይገባል ከሚል የተነደፈ አሰራር ነው፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ሁኔታ መለስ ስንል ሊሞቱ የደረሱ ነገር ግን ከሞት የተረፉ እናቶችን ሁኔታ መንግስት ሆስፒታች ውስጥ በምእራብ ሸዋ ዞን ማለትም በመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል የተመለከቱት እነ ነጋሽ ዋቅጅራ (MSc, Ass Prof) ናቸው፡፡ ባለሙያዎቹ እ.ኤ.አ February, 2021 በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር አመታዊ ጉባኤ ላይ ያቀረቡት መረጃ እንደሚከተለው ነበር፡፡
በተለያዩ ጥናቶች እንደተጠቆመው በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎችና የጤና ተቋማት ከፍተኛ የሆነ የእናቶች ሞት ቢኖርም በየማእከሉ ትክክለኛው ቁጥር ተገልጾ ወይንም ተመዝግቦ ስለማይገኛ በጥናት ትክክለኛውን መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑ አልቀረም፡፡ በዚህም ምክንያት ችግሩን ሊያመጡ የሚችሉ አመላካች ነገሮችን ለማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነው እንደ ዳሰሳ ጥናት አቅራቢዎቹ እምነት።
ለሞት የደረሱ እናቶች ግን ከሞት የተረፉት ሁኔታ ማለትም የደረሰባቸው ችግር ለእናቶች ሞት ምክንያት የሚሆኑትን ለማግኘትና ጥራት ያለው የጽንስና ማህጸን ሕክምና አገልግሎት መኖር አለመኖሩን በየጤና ተቋማቱ ለመመልከት የመረጃዎች መጠናቀር ይረዳል፡፡ የእናቶች ሞት አጋጣሚው ዝቅ ያለ ቢሆንም ለሞት የደረሱ ነገር ግን ከሞት የተረፉ እናቶች የጤና ሁኔታ እና ነገር ግን ሊሞቱ የደረሱበት ምክንያት እንዲሁም የሚሰጣቸው የጤና አገልግሎት መሻሻል እና ጥራት ያለው ጽንስና ማህጸን አገልግሎት መኖር ያለመኖር ሊፈተሸ የሚገባው መሆኑን የሚያመላክት አጋጣሚ ተብሎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡
በምእራብ ሸዋ ዞን ማለትም በመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ለሞት የደረሱ ነገር ግን ከሞት የተረፉ እናቶችን ሁኔታ በሚመለከት የተለያዩ ጥናቶችን የተመለከቱት እነ ነጋሽ ዋቅጅራ (MSc, Ass Prof) እ.ኤ.አ February, 2021 እንደገለጹት እ.ኤ.አ ከጁን እስከ ኦክቶቨር 2019 ከተመለከቱዋቸው ውስጥ እናቶቹ ወደሆስፒታል የገቡት ለሞት የሚያደርስ ሁኔታ ላይ ሆነው ሲሆን ለወሊድ የደረሱ ወይንም ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የጤና ችግር የደረሰባቸው ነበሩ፡፡
በኢትዮጵያ በምእራብ ሸዋ የህዝብ ሆስፒታሎች ውስጥ ለህክምና አገልግሎት የደረሱት ሊሞቱ የነበሩና በሁዋላ ግን የተረፉ እናቶች በተለያዩ መመዘኛዎች ውስጥ የሚገቡ ነበሩ፡፡ መመዘኛዎ ቹም የእናቶቹ ሁኔታ፤ የትምህርት ደረጃ ፤በምን ሁኔታ ላይ ሆነው ወደሆስፒታል እንደደረሱ፤ የወር ገቢያቸው እና ወደሆስፒታል ለመድረስ ካሉት መዘግየቶች የመጀመሪው እና ሁለተኛው መዘግየት የሚመለከታቸው መኖራቸውን የተመለከተ ነበር፡፡
የትምህርት ሁኔታ፤
ሊሞቱ ደርሰው ወደሆስፒል የመጡት እናቶች በሁዋላ ግን የተረፉት ብዙዎች ማንበብ መጻፍ የማይችሉ እና የተወሰኑት የመጀመሪ ደረጃ ትምህርት አልፎ አልፎ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ የደረሱ ነበሩ፡፡ በኮሌጅ ደረጃ እና ከዚያ በላይ ግን እጅግ ዝቅተኛ እናቶች ነበሩ፡፡
በትምህርት ላይ የነበሩ፤
በምእራብ ሸዋ የመንግስት ሆስፒታሎች በ እነ ነጋሽ ዋቅጅራ (MSc, Ass Prof) በተደረገ የዳሰሳ ጥናት እንደታየው የቤት እመቤት ከነበሩት እናቶች ይልቅ በትምህርት ላይ የነበሩ ሴቶች በአብዛኛው በእርግዝና ቸው ምክንያት በደረሰ የጤና ችግር ምክንያት ለሞት ደርሰው ነገር ግን የተረፉ ነበሩ። ምናልባትም ተማሪዎች በኢኮኖሚው ዘርፍ ለትምህርት ቤት በሚከፍሉት ወይ ንም ለተለያዩ ነገሮች የሚጠቀሙበት በመሳሰሉት በሌሎች ላይ ጥገኛ የመሆን እድል ስለአላ ቸው ጤናቸውን በሚመለከት በውሳኔ ሰጭነቱ ላይ መዘግየትን ሊያስከትልባቸው ስለሚችል ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡
ወደሆስፒታል ለመግባት አለመረቁረጥ፤
ወደሆስፒታል የመግባት እድሉን በተረጋጋ ወይንም በቁርጠኝነት የማያከናውኑት በተረጋጋ ወይን ቁርጠኝነት ባለው ሁኔታ ከሚያደርጉት ይልቅ ለሞት የደረሱ ግን በሁዋላ የሚድኑት እናቶች ቁጥራቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ለዚህ በምክንያትት የሚጠቀሰውም በተረጋጋ ሁኔታ ወደ ሆስፒታል የማይቀርቡት እናቶች ምናልባትም ከፍ ያለ ሕመም እየተሰማቸውም ተገቢውን ምርመራ አለማድረግ ወይም ሆስፒታል በሚደርሱበት ወቅት የከፋ ሕመም ገጥሞአቸው ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ፡፡
የወር ገቢ፤
ጥናቶች እንደሚያሳዩት አነስተኛ የወር ገቢ ያላቸው እናቶች ከፍ ያለ ገቢ ካላቸው ይልቅ በእርግዝናቸው ወቅት ለሞት የሚደርሱበት ደረጃ ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ ተረጋግጦአል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የገቢያቸው ዝቅተኛ መሆን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታቸውን ስለሚጎዳ ለስነተዋልዶ ጤና ትኩረት እንዲያደርጉ እድሉን ስለማይሰጣቸው ነው፡፡ ጥሩ የወር ገቢ ያላ ቸው ውሳኔ ለመስጠትና ወደሕክምና ተቋም ለመሄድ አቅም ስላላቸው መዘግየቶችን ለማስወገድ እና የተሸለ የጤና አገልግሎት ለማግኘት ይችላሉ፡፡
እናቶች የኑሮ ሁኔታቸው፤ ትምህርታቸውእና ወደሆስፒታል ለመግባት መቁረጣቸው፤ ወርሃዊ ገቢ የመሳሰሉት ወደ ሆስፒታል ሳይሄዱ በቤታቸው የመጀመሪያውን መዘግየት እንዲያደርጉ፤ ወደሆስፒታል የሚሄዱበት መንገድ ምቹ ባለመሆኑ ወይንም መጉዋጉዋዣ በመቸገር በመሳሰ ሉት ሁለተኛው መዘግየት የሚደርስባቸው በመሆኑ እናቶች ለሞት ደርሰው ለጥቂት የሚተር ፉባቸው ወይንም የሚሞቱበት አጋጣሚ ተስተውሎአል እንደ ጥናት አቅራቢዎቹ፡፡
ስለዚህም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እናቶች በእርግዝና ፤በወሊድ ወይንም እርግዝናው 42 ቀን ሲሆነው ጀምሮ ሊከሰት የሚችለውን ከሞት አፋፍ መድረስ ለማስቀረት የእናቶችን አቅም በማጎልበቱ ረገድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራት ይጠበቅበታል እነ ነጋሽ ዋቅጅራ (MSc, Ass Prof) እንደገለጹት፡፡  

Read 11657 times