Saturday, 15 May 2021 15:31

“የጓሮ ማህበረሰብ” ግሩፕ ያዘጋጀው ኤግዚቢሽን ዛሬ በፈንዲቃ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ በመጠቀም በሚል የተከፈተውና በትንሽ ቦታ ላይ ጓሮን የማሳመርና አትክልቶችን የመንከባከብን ግንዛቤ ለማስፋት የተመሰረተ “የጓሮ ማህበረሰብ” (ሆም ጋርዳኒንግ ኮሙኒቲ) ያዘጋጀው የጋርዳኒንግ ኤግዚቢሽን ዛሬ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንዲቃ የባህል ማዕከል ይከፈታል።
በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ20 ሺህ በላይ ተከታይና አባላትን ያፈራው “የጓሮ ማህበረሰብ” የፌስቡክ ግሩፕ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ስለ ጓሮ አትክልት በትንሽ ቦታ ላይ እንዴት አትክልት ተክሎ ለምግብነትም ሆነ ለግቢ ማሳመሪያነት ማዋል እንደሚቻል፣ ስለተለያዩ የምግብ አትክልቶችንና የግቢ ማሳመሪያዎች ግንዛቤ ሲፈጥር ግንዛቤን ሲያገኝ እንደቆየ የግሩፑ መስራች ጋዜጠኛ ትዕግስት ታደለ ተናግራለች። ኮቪድ-19 ወደ ሀገራችን መግባቱን ተከትሎ በተፈጠረ የገበያ እጥረት ሀሳቡ እንደመነጨ የምትገልፀዋ ትዕግስት፣ ይህ እንዲለመድ በግሩፑ ሲሰራ መቆየቱን ገልፃ ዛሬ በሚከፈተው ኤግዚቢሽን የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኝ አምራቾች፣ የአበባ እቃ አምራቾች፣ የችግኝ አፈር መያዣ ላስቲክ አምራቾችና በአጠቃላይ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ሁሉ ተሳትፈው ልምድ ልውውጥ የሚደረግበት መድረክ በመሆኑ፣ ለአንድ ቀን ብቻ በሚቆየው በዚህ ኤዝቢሽን ላይ  ሁሉም እንዲሳተፍ ጋዜጠኛዋ ጥሪ አቅርባለች።


Read 10909 times