Saturday, 15 May 2021 15:26

የእስክንድር ነጋ “ድል ለዴሞክራሲ” መፅሀፍ ዛሬ ገበያ ላይ ይውላል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) ፓርቲ መስራችና ሊቀመንበር የሆነውና አሁን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኘው የጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ “ድል ለዴሞክራሲ” መፅሐፍ ዛሬ በገበያ ላይ ይውላል፡፡ የመጽሀፉ ስብስብ ፅሁፎች በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የፃፋቸው እና ከዚያው የወጡ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ ፅሁፎች በአገራችን የፖለቲካ ውስብስብ ችግሮች እና መፍትሄ  ይሆናሉ ያላቸውን ሀሳቦችን ያመላከተበት ስለመሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በ272 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ በ230 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በሁሉም የመፅሀፍት መደብሮችና በአዟሪዎች እጅ ገብቶ ለአንባቢያን እንደሚደርስ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
የባልደራስ ሊቀመንበሩ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው ግርግር ለእስር የተዳረገ ሲሆን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ሲሆን እስከአሁን ፍርድ ያልተፈረደበት መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡


Read 4249 times