ከኢትዮጵ ጋዜጣ ጀምሮ የህወሃትን ምስጢሮች እስከ ዛሬም ድረስ በማጋለጥ የሚታወቀውና በቅርቡም የትግራይ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ የተሾመው የጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያም “ከህወሃት ጓዳ” መፅሀፍ በቀጣዩ ሳምንት ለንባብ ይበቃል። መፅሐፉ በዋናነት ለ27 ዓመታት /ኢህአዴግ፣ ከደደቢት እስከ አራት ኪሎ ቤተመንግስት እና በመላ ሀገሪቱ የፈጸማቸው ያላቸውን ግፍና ዝርፊያዎች ጋዜጠኛው በመፅሐፉ መተንተኑም ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም አግአዚ፣ ደፋሪዎቹ ሴት የብርጌድ መሪዎችና የ36 ሺህ ታጋዮችን አሳዛኝ ታሪክ በመተንተን ይህ ታሪክ ለትውልድ በማስረጃነት ተሰንዶ እንዲቀመጥ ጥረት ማድረጉም ታውቋል። በ216 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ፣ በ300 ብር ለገበያ እንደሚቀርብም ታውቋል።