Monday, 17 May 2021 15:36

የሰበታው ቱሉ መገርሳ ሆቴል ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በሰበታ ከተማ ቀበሌ 04 የሚገኘው “ቱሉ መገርሳ ኢንተርናሽናል ሆቴል” ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት እንደሚመረቅ ወጣቱ ባለሃብት አቶ ጅሩ መገርሳ ገለፁ፡፡ በቅርቡ ከሌላ ባለ ሃብት በ150 ሚ.ብር የተገዛውና ለእድሳቱ 100 ሚ.ብር የተመደበለት ሆቴሉ ከ5 ሺህ ካ.ሜ በላይ በሆነ ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን 54 አልጋዎች እስከ 2000 የሚደርስ ሰው የሚይዙ  የስብሰባና የሰርግ አዳራሾች፣ ስቲምና፣ሳውና ባዝ፣ የወንዶችና የሴቶች የውበት ሳሎኖች፣ የመዋኛ ገንዳ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ሆቴል ሊያሟላ የሚገገባውን  ያሟላ ነው ተብሏል፡፡ አሁን በሙሉ አቅሙ ስራ ሳይጀምር 182 ሰራተኞችን ቀጥሮ  የሚያሰራው ይሄ ሆቴል፤ እድሳቱ ሲጠናቀቅና በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር፣ የሰራተኞቹን ብዛት ወደ 265 እንደሚያሳድግ ባለሃብቱ፣ የሆቴሉ ማናጀርና የባለሃብቱ አማካሪዎች ምረቃውን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ሆቴሉ በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮችንም ከግምት ውስጥ በማስገባት ከ1 ሺህ በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ስጋ ቤትና አዳራሽ ፣የልጆች መጫወቻ፣ ድራፍት ቤት፣የኦሮሞ የባህል ምግብ አዳራሽ እየተሟሉለት ነው ተብሏል፡፡ በቀጣይም አራት ደረጃውን የጠበቁ ሬስቶራንቶች ይኖሩታል ተብሏል፡፡ በምረቃው ሳምንት ከ15-20 ሺህ ሰው ይታደማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የተናገሩት የሆቴሉ ሃላፊዎች፤ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ለዘጠኝ ቀናት መራዘሙን በያንዳንዱ ቀናት ከ1500-2000 ሰዎች ብቻ እንደሚያስተናግድ ተገልጿል፡፡


Read 1615 times