Print this page
Monday, 17 May 2021 16:13

የመጀመሪያው ዙር ሃገር አቀፍ የቢዝነስ ማሻሻያና ገበያ ትስስር ዎርክ ሾፕ ተካሄደ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በጢስ አባይ የኢኮኖሚ ልማት፣ ቢዝነስና ኢንቨስትመንት አማካሪ ድርጅት አዘጋጅነት የተሰናዳው የመጀመሪያው ዙር ሀገር አቀፍ የቢዝነስ ማሻሻያ ገበያ ትስስር መፍጠሪያ ዎርክ ሾፕ ባሳለፍነው ሳምንት በጊዮን ሆቴል ተካሄደ፡፡ አማካሪ ድርጅቱ፤ በዎርክሾቱ በሆቴልና ማኒፋክቸሪንግ ዘርፎች መነሻነት የተጠናው ቅድመ ዎርክ ሾፕ፣የኢትዮጵያ ገበያ በተለያዩ ችግሮች የተተበተበ በመሆኑ አስቸኳይ ፖሊሲ ሊወጣለት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
በአማካሪ ድርጅቱ የኦኮኖሚ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪና የወርክሾፑ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መንገሻ አበበ ሞሴነህ፤ የአሰራር ምልከታ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን በመጠቀም 50 ሆቴሎችን፣50 ኢንዱስትሪዎችንና 50 ተጠቃሚዎችን በአላማ ተኮር የናሙና ዘዴ ያጠኑትን የማርኬቲንግ ጥናት በወርክሾፑ ያቀረቡ ሲሆን በምርት እጥረት፣በምርት ጥራት መጓደል፣ ኢኮኖሚያዊ ባልሆነ የምርት ዋጋ ጭማሪና መሰል ችግሮች ሳቢያ ፈተና ውስጥ የገባውን የኢትዮጵያ ገበያ፣ የህዝብ ብሶት ተከትሎ ከሚመጣ የኢንስፔክሽን እና የሬጉሌሽን የቁጥጥር ሥራ ይልቅ የሀገሪቱን የንግድና ኢንቨስትመንት አቅም መሰረት ያደረገ፣ በአመራረትና በግብይት ሂደት የምርት ጥራትን ያመለከተ፣የምርት ስርጭት ፍትሀዊነት፣ከባቢያዊና የፍጆታ ፍላጎትን፣ ፍትሃዊ የመሸጫ ዋጋ ደረጃንና የማርኬቲንግ ማበረታቻ ሥርዓትን የሚያመለክት የማርኬቲንግ ፖሊሲ አለመኖሩ ገበያው ቅጥ እንዲያጣ ማድረጉን በጥናታቸው አመልክተዋል፡፡
በተቀያያሪ የገበያ ፍሰት ውስጥ በመሆናችን ነው ከምርትና አገልግሎት የምናገኘው እርካታም በየጊዜው እየተቀያየረና በኑሮ ውድነት እየተለበለብን ሲሉ የጥናቱ አካል የሆኑ ተጠቃሚ የማህበረሰብ ክፍሎች መናገራቸውም በጥናት ግኝቱ ተካቷል፡፡


Read 1717 times
Administrator

Latest from Administrator