ጊዜ ባርና ሬስቶራንት ዛሬ ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ ልዩ የሙዚቃ ድግስ ማስናዳቱን ገለፀ። በዚህ የሚዚቃ ድግስ ድምፃዊ ታረቀኝ ሙሉ (በባይተዋር ጎጆ)፣ አዲስ ጉልሜሳ (የማህሙድ)፣ አብነት ደምሴ (የማሪቱ) እና ዋሲሁን ረታ (የሙሉቀን) ድምፃዊያኑ ከማህሌት ባንድ ጋር በመጣመር በቀጥታ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ዳዊት ፍሬው ሀይሉ ሳክስፎን እንደሚጫዎትም የጊዜ ባርና ሬስቶራንት ሃላፊዎች ገልፀዋል።
በዚህ ልዩ ምሽት ከወዳጅ ዘመድ ጋር ቦሌ ማተሚያ ቤት በሚገኘው ጊዜ ጀርባ ባርና ሬስቶራንት መጥተው በመታደም አስደሳች ጊዜ እንዲያሳልፉ ግብዣ የቀረበ ሲሆን የሙዚቃ ድግሱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ፕሮቶኮል በጠበቀ መልኩ እንደሚካሄድና ቀድመው የመጡ ብቻ እንደሚስተናገዱ ለማወቅ ተችሏል።
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል