Saturday, 22 May 2021 12:48

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኪነ-ጥበብ ስራዎቹ ተዘከረ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

  “ሰው ለሰው” እና “ዘመን” በተሰኙት ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎቹ፣ “ዙምራ” በተሰኘው ፊልሙና በሬዲዮና በመድረክ ድራማ ድርሰቶቹ ዕውቅናን ያተረፈውና በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱን ያጣው አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለፈው ሀሙስ ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ተዘከረ።
በሥነ-ስርዓቱ ላይ ስራዎቹን የሚገልፅ አጭር ዘጋቢ ፊልም፣ የህይወት ታሪኩ በፅሁፍ ከ”ሰው ለሰው” ተከታታይ ድራማው ላይ የተቀነጨበ ተውኔት በተዋንያኑና ሌሎችም ጥበባዊ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን መስፍን ለሀገር ኪነ-ጥበብ ለዋለው ውለታና ታታሪነቱ ምስጋና ቀርቦለታል።  
በዚህ የአርቲስቱ የዝክር መርሃ ግብር ላይ ቤተሰቦቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የመንግስት ስራ ሃላፊዎችና የኪነ-ጥበብ አድናቂዎች የታደሙ ሲሆን ለከያኒው ያላቸውን አክብሮትና ፍቅር ገልፀዋል።

Read 21600 times