Saturday, 05 June 2021 11:57

“ልብ አልባው ዶክተር” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የመፅፉ ሽያጭ ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለካንሰር ህሙማን ይውላል

            መኖሪያዋን በአሜሪካ አትላንታ ጆርጂያ ባደረገችው ደራሲና የፊልም ባለሙያ አስቴር አበበ (ቲጂ) የተፃፈውና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው “ልብ አልባው ዶክተር” ረጅም ልቦለድ መፅሀፍ ለንበባ በቃ፡፡
ደራሲዋ የመፅሀፉ ሽያጭ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ላሉ ካንሰር ህሙማን መርጃ እንደሚውል ገልፃለች:: መፅሀፉ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የፍቅርን ሀያልነት፣ በተለይ በስደት ዓለም ለሚኖሩ የጓደኝነት ልዩ ጣእም፣በልዩነት የተጣምሮነትን አንግልትና በዚያ ውስጥ ያለውን ውበት፣የመኖር ምሬትና አርካታ፣ በአጠቃላይ የህይወትን ዝብርቅርቅ ገፅታ እያንፀባረቀና ልብ እያንጠለጠለ ብዙ የሚያስተምር ታሪክ ነው ተብሎለታል፡፡
ረጅም ልቦ ወለዱ በ426 ገፅ ተቀንብቦ በ350 ብርና በ20 ዶላር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ገቢው ለበጎ አድራጎት እንዲውል ደራሲዋ በወሰነች ጊዜ ረጅሙን ፅሁፍ ፣በኮምፒዩተር የመተየቡንና የማስተካከሉን ሥራ በትጋት እንድትወጣ እንደረዳት ደራሲዋ በመፅሀፍ መግቢያ አስፍራለች፡፡

Read 1694 times