Print this page
Saturday, 05 June 2021 11:57

“የወርቅ ዘንግ” መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የመምህር መስፍን ሰለሞን ስራ የሆነው “የወርቅ ዘንግ” መፅሀፍ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር እንደሚመረቅ የምርቃቱ አዘጋጅ ሰምና ወርቅ ኢንተርቴይመንት አስታወቀ፡፡
በእለቱ በመፅሐፉ ላይ ዳሰሳና አስተያየት፣ ግጥም፣ከመፅሀፉ የተመረጠ ታሪክና መነባንብ ለታዳሚ ይቀርባል የተባለ ሲሆን፤በመፅሀፉ ላይ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ መጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)፣ ጌትነት ፈለቀ (ዶ/ር)፣ ወዳጄነህ መሃረነ ( ዶ/ር) ፣ደራሲና ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠና ደራሲ መሃመድ አሊ ቡርሃን ደሳሳና አስተያየት እንደሚሰጡ ሲሆን ገጣሚያኑ መቅደስ ጀምበሩ፣ ኤፍሬም ስዩምና ደሳለኝ ግርማ ግጥም፣አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ከመፅሀፉ ምንባብ አርቲስት ሱራፌል ተካ መነባንብ ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ የመድረኩ አጋፋሪ ኮሜዲያን አዝመራው ሙሉ ሰው መሆኑም፣ ታውቋል፡፡

Read 1702 times