Print this page
Saturday, 05 June 2021 12:00

“ፈንጠዝያ” የካርቶን ስዕሎች ስብስብ መፅሐፍ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በሀገራችን ደረጃ የካርቱን ስዕሎችን በመሳልና የሀገርን ባህል፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁነቶችን በካርቶን ሥዕል በመግለፅ አቻ ያልተገኘለት ሠዓሊ አለማየሁ ተፈራ “ፈንጠዝያ” በሚል ርዕስ ያሰባሰባቸው የካርቶን ስዕሎች የያዘ መፅሀፍ ከትላንት በስቲያ ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኤሊያ ሆቴል አስመረቀ፡፡
በምርቃቱ ላይ እውቅ ሰዓሊያን ፣በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  የአለ የሥነ- ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ከፍተኛ ሃላፊዎች፣የስዕል አፍቃሪያንና የሰዓሊው አድናቂዎች ታድመዋል፡፡ ሰዓሊው “ፈንጠዝያ” በሚል ርዕስ  ለህትመት ያበቃቸው የካርቶን ሥዕሎች በአሁኑ ወቅት ሀገራችን እየተጓዘች ያለችበትን ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ውጣ ውረድ በተዝናኖት መልሰን እንድንቆምበት የሚያደርግ የፈጠራ ውጤት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በዕለቱ “ፈንጠዝያ የተሰኘው የካርቶን ስዕል አውደ ርዕይም ተከፍቶ ለእይታ በቅቷል፡፡ ሰዓሊ አለማየሁ ተፈራ የሀገራችንን የካርቶን ስዕል በእጅጉ እንዳሳደገውና እንደተራቀቀበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ “አለ” የስነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ አዳነ ድልነሳው ተናግረዋል፡፡

Read 1648 times