Print this page
Sunday, 06 June 2021 00:00

“አንዱ ለሁሉ” ሙዚቃዊ ተውኔት ሰኞ ለእይታ ይቀርባል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ትምህርት ቤት ሀላፊና ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱና ቻላቸው ፈረጅ ፀሀፊነትና አዘጋጅነት የተሰናዳው “አንዱ ለሁሉ” የተሰኘ ሙዚቃዊ ተውኔት ከነገ በስቲያ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተመርቆ ለእይታ ይበቃል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በዳመራ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ትብብር የተሰራው ሙዚቃዊ ተውኔቱ፣ በሀገር አንድነትና ፍቀር ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነም የሁነቱ አስተባባሪ ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አስታውቋል፡፡
ቴአትሩን ለመመልከት የመግቢያ ዋጋው በሠዓቱ በቦታው መገኘት ነውም ተብሏል፡፡

Read 10435 times