Sunday, 06 June 2021 00:00

የደረጀ በላይነህ “ሒሳዊ ደሳሳ” ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የእውቁ ደራሲና ሀያሲ ደረጀ በላይነህ አስረኛ ስራ የሆነው “ሒሳዊ ዳሰሳ” መፅሀፍ ሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጊዮን ሆቴል በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ ይመረቃል፡፡ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ድግሶች የሚቀርቡ ሲሆን የመፅሀፍ ዳሰሳ፣ ግጥሞች፣ ወግ፣ ከመፅሀፍፉ የተመረጡ ታሪኮች፣ ሙዚቃና ደራሲውን የማስፈረም ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን የምረቃ መርሃ ግበሩ አዘጋጅ “ፈትል ህትመትና ማስታወቂያ” አስታውቋል፡፡
በዕለቱም ገጣሚና ደራሲ አበረ አዳሙ፣ ሰዓሊና ገጣሚ በቀለ መኮንን፣(ረ/ፕ). አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ፣ ጋዜጠኛ ፍቅር ይልቃል፣ገጣሚ በላይ፣ በቀለ ወያ፣ ገጣሚና ደራሲ ተስፋዬ ማሞ፣ ዘመዱ ደምስስ (ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ) እና አርቲስት ፈለቀ አበበ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
መድረኩን ጋዜጠኛ ሃይለሚካኤል ዴቢሳ የሚያጋፍር ሲሆን፣ድምፃዊ ባልከው የሙዚቃ ሥራውን ያቀርባል ተብሏል፡፡ ደራሲና ሀያሲ ደረጀ በላይነህ ከዚህ ቀደም “ብልጥ ጀምበር”፣ “የአዳም ድንኳን”፣ “የእድሜ መንገድ”፣ “የተስፋ ቀን”፣ “የናፍቆት ጥላዎች”፣ “የአደራ ቃል”፣ “የማይጠፋ እሳት”፣ “የደመና ሳቆች” እና “ትንታጎቹ” የተሰኙ ዘጠኝ መፅሀፍትን ለንባብ ማብቃቱ የሚታወስ ሲሆን ሰኞ የሚመረቀው “ሂሳዊ ዳሰሳ” አስረኛ ሥራው ነው፡፡

Read 10670 times