Sunday, 06 June 2021 00:00

ብራና የኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     ወርሃዊው ብራና የኪነ-ጥበብ ምሽት የዚህ ወር መሰናዶ “ሀገር ማለት” በሚል መሪ ቃል ከነገ በስቲያ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
በዕለቱ ሀገራዊ ጉዳዮች በምሁራን የሚነሱ ሲሆን፣ እውቁ ፖለቲከኛ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)፣ የሀበሻ ጀብዱ መፅሀፍ ተርጓሚ ተጫነ ጀብሬ መኮንን፣ መምህርትና ፀሀፊ መስከረም አበራ፣ገጣሚያኑ ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙና ኤሌሊያስ ሽታሁን፣ ህይወት አዳነና ጋዜጠኛ ግሩም ጫላ፣ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
በዕለቱ አበበ ቶሎ ፈይሳ (አቤ ቶኪቻው) ወግ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ሻሎም ለኢትዮጵያ የባህል ቡድን መሰናዶውን በሙዚቃ እንደሚያደምቅና  መድረኩን ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ እንደሚያጋፍር ተገልጿል፡፡ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር እንደሆነ የተነገረለት የኪነ- ጥበብ ምሽቱ ትኬቶቹ በጃፋር መፃፍት መደብር እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

Read 10518 times