Saturday, 05 June 2021 12:23

91 በመቶ የትግራይ ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

       በግጭት ውስጥ በሚገኘው የትግራይ ክልል፤ ህዝብ 91 በመቶ ዜጎች በአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጠባቂነት መዳረጉን የተባበሩት መንግስታት ከትናት በስቲያ ሃሙስ ባወጣው አስቸኳይ መልዕክቱ አሳስቧል፡፡
በትግራይ አሁንም ድረስ ግጭቶች አለመቆማቸውና ለእርዳታ አቅርቦት አመቺ ሁኔታ አለመፈጠሩ የዜጎችን ስቃይ እያከፋው መሆኑን የጠቆመው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም፤ ለጋሽ አካላት የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጠይቋል፡፡
ባለፉት 7 ወራት በግጭት የዘለቀው የትግራይ ክልል፤ ከ5.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ በአጠቃላይ ለአስቸኳይ እርዳታ አቅርቦቱ ከ2 መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል፡፡
የዓለም የምግብ ፕሮግራም በመግለጫው፤ “በትግራይ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ የከፋ ረሃብ ይከሰታል የሚል ስጋት አለን” ብሏል፡፡
አለማቀፍ ተቋማትና የረድኤት ድርጅቶች በዋናነት የእርዳታ አቅርቦት የሚቀላጠፍበትን ሁኔታ ላይ  አተኩረው እንዲሰሩ፤ የጠየቀው ተቋሙ ኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ በተቻለው አቅም ሚሊዮኖችን ተደራሽ ያደረገ የምግብ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን መረዳት ተችሏል ብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት አልሚ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ህፃናትና እናቶች አቅርቦቱን ማግኘት የቅንጦት ያህል ሆኖባቸዋል ይላል-ሪፖርቱ ያመለከተው፡፡
የአሜሪካ መንግስትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በክልሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጎ፣ ለዜጎች እርዳታ ያለአንዳች ገደብ በነጻነት የሚቀርብበት ሁኔታ መመቻቸት ይገባዋል ሲል አሳስቧል በሪፖርቱ፡፡

Read 816 times