Print this page
Saturday, 05 June 2021 12:28

በ5 ክልሎች በሚገኙ 39 ምርጫ ክልሎች ሠኔ 14 ምርጫ አይደረግም

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

     ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚከናወነው አጠቃላይ ሀገር አቀፍ ምርጫ፣ በ5 ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 39 የምርጫ ክልሎች ምርጫው እንደማይካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡
በፀጥታ ችግርና  ቁሳቁስ በወቅቱ ባለመሰራጨቱ እንዲሁም ከሌሎች ምክንያቶች ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ሰባት፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ አራት፣ በሱማሌ ክልል 14፣ በአማራ ክልል 7 ፣ በደቡብ 7 የምርጫ ክልሎች ላይ ሰኔ 13 ቀን 2013 ምርጫ እንደማይካሄድ ቦርዱ አስታውቋል፡፡
በቤንሻንጉል ክልል በመተከል፣ ሺናሻ ልዩ፣ ካማሺና  ዳለቲ የምርጫ ክልሎች ምርጫው እንደማይካሄድባቸው ተጠቁሟል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በቤጊ፣ ሰኞ ገበያ፣ አያና፣ ገሊላ፣ አሊቦ ፣ ጊዳሚና ኮምቦልቻ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫውን እንደማካሄድ የቦርዱ መረጃ ያመለክታል፡፡
በደቡብ ክልል በተመሳሳይ በ7 የምርጫ ክልሎች ላይ ድምፅ በእለቱ የማይሰት ሲሆን ከእነዚህም ሸኮ ልዩ ምርጫ ክልልና ቴፒ ምርጫ ክልል በአካባቢው ባለው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ምርጫው በእለቱ አይከናወንም ተብሏል፡፡
ቦርዱ በአካባቢዎቹ ያሉ ሁኔታዎችን እየገመገመ ምቹ ሁኔታ ሲፈጠር ምርጫውን እንደሚያስፈጽም አስታውቋል፡፡

Read 13618 times