Print this page
Saturday, 05 June 2021 12:34

የኢዜማ “አዲስ አበባ ጠይቂ” መርሃ ግብር ዛሬ ይካሄዳል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

  የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ በማናቸውም ጥያቄዎች ላይ መልስና ማብራሪያ የሚሰጥበት መርሃ ግብር በዛሬው እለት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
“አዲስ አበባ ጠይቂ” በሚል መርህ የተዘጋጀው የፓርቲው የቀጥታ ጥያቄና መልስ መርሃ ግብር፤ የከተማዋ ነዋሪዎች ማናቸውንም ኢዜማን የተመለከቱ ጥያቄዎች ለመሪዎቹ በቀጥታ በማቅረብ ምላሽ የሚያገኙበት ይሆናል ብለዋል- የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ፡፡
በመድረኩ ላይ የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና አቶ ክቡር ገናን ጨምሮ ሌሎች  ከፍተኛ አመራሮች ከታዳሚዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ኢዜማ ይህን የህዝብ ጥያቄና መልስ መድረክ ያዘጋጀው በሚዲያ ተደራሽ ያልሆኑ የህዝብ ጥያቄዎች ወደ መድረክ ቀርበው ምላሽ እንዲያገኙ በማሰብ መሆኑን አቶ ዘላለም አብራርተዋል፡፡
በመድረኩ ማንኛውም ለኢዜማ ጥያቄ አለኝ የሚል ዜጋ ተገኝቶ ጥያቄ ያለገደብ ማቅረብ ይችላል ተብሏል፡፡ መርሃ ግበሩ ከጠዋቱ 3 ሠዓት ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ይካሄዳል፡፡


Read 13310 times