Print this page
Saturday, 05 June 2021 14:28

በ5 ቢ.ብር በደብረ ማርቆስ የተገነባው የዘይት ፋብሪካ ሰኞ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)


            እውቁ ባለሃብት አቶ ወርቁ አይተነው በ5 ሚ.ብር ወጪ በደብረ ማርቆስ ያስገነቡት WA ዘይት ፋብሪካ ከነገ በስቲያ ሰኞ ይመረቃል፡፡ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ደብረ ማርቆስ ውስጥ በሊዝ በተገኘ 101 ሺህ 103 ካ.ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ግንባታው አራት ዓመታትን የፈጀው የዘይት ፋብሪካው፤ የግንባታ፣ የማሽነሪና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ገጠማው ተጠናቆ ወደ ምርት መግባቱ ተገልጿል፡፡ የሰሊጥ፣ የአኩሪ አተር፣ የኑግ፣ የሱፍና የለውዝ  የምግብ ዘይት ከነዚህም በተጨማሪ ድፍድፍ የፓልም ዘይት ከውጭ በማስገባትና በግብዓትነት በመጠቀም አጣርቶ ያለቀለት ዘይት ለገበያ እንደሚያቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት ለ1 ሺህ 500 ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ለ3 ሺህ ሰዎች የስራ እድል እንደሚጥርም ተገልጿል፡፡
ፋብሪካው በዋናነት በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የቅባት እህሎችን ታሳቢ አድርጎ የተገነባ ሲሆን፣ በፋብሪካው አካባቢና በአቅራቢያ ቦታዎች ካሉ አርሶ አደሮች ጋር ትስስር በመፍጠር ብሎም ምርታማነት እንዲጨምሩ ድጋፍ በማድረግ፣ አርሶ አደሮች የቅባት እህሎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለፋብሪካው እንዲያቀርቡና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ በኩል ሰፊ የስራ እድል መፈጠሩም ተጠቁሟል፡፡
ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ የአገር ውስጥ ገበያውን በማረጋጋት ማህረሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን ከዚህም በላይ አገሪቱ እስከዛሬ የዘይት ምርቶችን ለማስገባት የምታወጣውን የውጪ ምንዛሬ በማዳን ለአገር ኢኮኖሚ  ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል፡፡
WA የዘይት ማምረቻና ማከፋፈያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በቀጣይ ባለ 1 ሊትር ፣ ባለ3 ሊትር፣ ባለ5 ሊትር፣ ባለ 10 ሊትርና ባለ 20 ሊትር ዘይት በከፍተኛ ጥራትና ቴክኖሎጂ አምርቶ እንደሚያቀርብ ተነግሯል፡፡
የዘይት ፋብሪካው የWA ኢንቨስትመንት ግሩፕ  አካል ሲሆን ኢንቨስትመንት ግሩፑ በአሁኑ ወቅት ወርቁ ሜካናይዝድ እርሻ፣ ወርቁ አስመጪና ላኪ ፣ ወርቁ ሪል እስቴት፣ ጎልድስታር አቪየሽን ፣ ወርቁ ፔትሮሊየም፣ WA የማዕድን ማውጣትና ማምረት፣ ወርቁ ትራንስፖርት፣ “ውሃሃ” የውሃ ማጣሪያና ማሸጊያ ፋብሪካ፣ “ሰላ ጎጃም” የዘይት ፋብሪካና WA የሲሚንቶ ፋብሪካን በአንድ ላይ እያስተዳደረ፣ እንደሚገኝና ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንደፈጠረ ተጠቁሟል፡፡ ፡፡

Read 1941 times
Administrator

Latest from Administrator