Saturday, 12 June 2021 12:46

የካስማሰ “አብረን አንድ ላይ ወደ ላይ” ኮንሰርት ዛሬ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)


          “ቀና ልብ” የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበም ባወጣ አጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያተረፈው ራፐር ካስማሰ “አብረን አንድ ላይ ወደ ላይ” የተሰኘው የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል ይካሄዳል፡፡
በዋልያ ቢራ ስፖንሰር የተደረገው ኮንሰርቱ፣ የኮቪድ 19ን መስፈርት በጠበቀ መልኩ እንደሚካሄድ የተጠቆመ ሲሆን፣ የወጣቱ ካስማሰ አድናቂዎች በሙዚቃ ድግሱ ጥሩ ጊዜን እንደሚያሳልፉ ይጠበቃል፡፡ ከካስማሰ በተጨማሪ እነ “አሀዱ”፣ “ዮሃን”፣ አዝማች፣ 251 እና “ቀጭን ጠጅ” ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

Read 1484 times