በየወሩ የሚካሄደው እና በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት የሚከወነው የዚህ ወር መሰናዶ “ሀገር ምን ትሻለች” በሚል መርህ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዕለቱም ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ መምህር ፋንታሁን ዋቄ፣ መምህር አገኘሁ አዳነ፣ ደራሲ መሃመድ አሊ ቡርሃንና መምህር መስፍን ሰለሞን ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን፣ አርቲስት ሱራፌል ተካና አርቲስት ካሌብ ዋለልኝ ወግ፣ ገጣሚያኑ ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙና ገጣሚ ተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሽ) ግጥም እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ በሻሎም ለኢትዮጵያ ሙዚቃ የሚታጀበው የኪነ- ጥበብ ምሽቱ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር እንደሆነም ታውቋል፡፡
Sunday, 13 June 2021 00:00
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና