Monday, 14 June 2021 00:00

የዳዊት ፍሬው ሀይሉ “የኢትዮጵያዊነት አሻራ” በሲዲ ሊመጣ ነው

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የእውቁ ፍሉት ተጫዋች ዳዊት ፍሬው ሀይሉ ስራ የሆነውና በአሁኑ ወቅት በአውታር መልቲ ሚዲያ ኦንላይን በሽያጭ ላይ ያለው “የኢትዮጵያዊነት አሻራ” በሲዲ ሊመጣ ነው፡፡
መታሰቢያነቱ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና 125ኛው የአድዋ ድል በዓል የሆነው ይሄው አልበም በውስጡ ከጃንሆይ ጊዜ ጀምሮ አባይን ለመገደብ የታሰበው ዕቅድ፣ ስለ ህዳሴው ግድብ ከቀድሞዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሮች መለስ ዜናዊ እና ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጀምሮ የተነገሩ ዋና ዋና ንግሮች፣ “አባይ ልብ ግዛ” የተሰኝ ግጥም “ለሁሉም ጊዜውን ይጠብቅለታል እና አልማዝ እንቁ መሳይን” ጨምሮ 13 ያህል በፍሉት የተጫወታቸው ሙዚቃዎች አባቱ ፍሬው ሀይሉ ጃንሆይ ያመሰገነበት የሙዚቃ ግጥምና ሌሎችም ታሪካዊ ነገሮችን አካቶ በቅርቡ በሲዲ እንደሚመጣ ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው ሀይሉ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
ዳዊት አክሎም የህዳሴውን ግድብ ለመገደብ ከተነሳንበት ጀምሮ በጠላት ጥርስ ገብተን ሳለ ኢትዮጵያዊያን ብዙ ማለት ሲገባን ዝም ማለታችን ስለቆጨው ይህን ስራ መስራቱን እና፣ በቅንብሩ ፈለቀ ሀይሉ፣ ሄኖክ መሃሪና ወንድሜነህ መሳተፋቸውን ገልጾ በቅርቡ በሲዲ እንደሚመጣ ገልጿል፡፡


Read 9423 times