Sunday, 13 June 2021 19:31

መንግስት ለጌርጌሴኖን 3 ሺህ ካ.ሜ ቦታ ፈቀደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ዛሬ የህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል
                       
            በ1998 ዓ.ም በሊቀ ህሩያን መለስ አየለ የተቋቋመውና 1ሺህ የሚጠጉ የአዕምሮ ህሙማንን ከጎዳናና ከሀይማኖት ተቋማት በር ላይ በማንሳት፣ ለ15 ዓመታት በአስቸጋሪ ቦታና የኪራይ ቤት የቆየው ጌርጌሲዮን የአዕምሮ መርጃ ማህበር ከመንግስት 3ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ አገኘ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የማህበሩን ጥረትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች በመመልከት ቦታውን ከሊዝ ነፃ ለማህበሩ በመስጠት ለህሙማኑ ማገገሚያ የሚሆን ህንጻ እንዲገነባበት በመፍቀዱ የተሰማቸውን ደስታ የማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ህሩያን መለስ አየለ ተናግረዋል፡፡
ዛሬ ረፋድ ላይ ማህበሩ ለህንጻው ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በመጣል ደስታውን እና ምስጋናውን ለከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ይገልጻል ተብሏል፡፡ በዚህ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ- ሥርዓትና የምስጋና መርሃ ግብር ላይ የጤና ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ክንቲባ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣የግልና የመንግስት ድርጅቶች፣ በአዕምሮ ጤና ላይ የሚሰሩ ሴክተር መ/ቤቶች የጤና ባለሙያዎችና የጌርጌሴኖን ቤተሰቦች  ሽሮሜዳ ቁስቋም ቤተ ክርስቲያን ዝቅ ብሎ በሚገኘኘውና በተረከበው ቦታ ላይ ይታደማሉ ተብሏል፡፡

Read 838 times