Saturday, 19 June 2021 16:35

እነ ጃዋር መሀመድ ለደህንነታቸው ሲባል ከምርጫ በኋላ ችሎት እንዲቀርቡ ታዘዘ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

 የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ፣ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳሳት ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት እነ ጃዋር መሀመድ ለማህበረሰቡና ለተጠርጣሪዎቹ ደህንነት ሲባል ጉዳያቸው ከምርጫ በኋላ እንዲታይና ለሰኔ 21 ቀን 2013  ችሎት እንዲቀርቡ ታዘዘ፡፡
የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከትናንት በስቲያ በዋለው ችሎት፤ተጠርጣሪዎቹ ለቀጠሮ ወደ ፍርድ ቤት በሚመላለሱበት ሂደት ውስጥ ከምርጫው ጋር በተያያዘ በሚከናወኑ የምርጫ ቅስቀሳና መሰል ሁኔታዎች ችግር እንዳይፈጠር በሚል ጉዳያቸው ከምርጫው በኋላ እንዲታይ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ችሎቱ ከትናንት በስቲያ በምስክር አሰማም ሂደት የተከሳሾች ጠበቆች ምላሻቸውን እንዲያቀርቡ በተሰጠ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰይሞ የነበረ ቢሆንም፣ በዕለቱ የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ ተከትሎ ለማህበረሰቡና ለተጠርጣሪዎቹ ደህንነት ሲባል ቀጠሮአቸው ከምርጫው በኋላ እንዲሆን በመደረጉ በዕለቱ ተጠርጣሪዎቹ በችሎት እንዳይቀርቡ መደረጉን ፍ/ቤቱ ገልጿል፡፡
የተከሳሽ ጠበቆች በምስክር አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ከዐቃቤ ህግ ለቀረበው አቤቱታ ምላሻቸውን እንዲያቀርቡ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ሰኔ 21 ቀን 2013 ለማየት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


Read 914 times