Saturday, 19 June 2021 17:13

በትግራይ ለጾታዊ ጥቃት አፋጣኝ ምላሽ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 ዶ/ር ተስፋነህ ፍቅሬ በ (ESOG) በኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር Emergency response to GBV (ለጾታዊ ጥቃት አፋጣኝ ምላሽ) የሚ ለው ፕሮጀክት ማናጀር ሲሆኑ በመስሪያ ቤቱ የሌ ሎች ፕሮጀክቶችም አስተባባሪ ናቸው፡፡ ለምሳሌም የጤና ባለሙ ያዎች ተከታታይ የሙያ ማጎል በቻ ፤ የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ እድሳትን በሚመለከት የሚሰጥ ስልጠና ፤ ከኦፕራ ሲ ዮን አገልግ ሎት ጋር በተያያዘ ደህንነቱ የተ ጠበቀ አሰራርን እውን ለማድረግ ጉድለቶ ችን ለማ ረም የሚያ ስችል ፕሮጀክት ጭምር አስተባባሪ ናቸው፡፡ ዶ/ር ተስፋነህ ፍቅሬ ለዚህ እትም የተ ጋበዙት Emergency response to GBV (ለጾታዊ ጥቃት አፋጣኝ ምላሽ) በሚለው ፕሮጀ ክት በትግራይ (One stop center) ለመጀመር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ወደ ትግራይ ሄደው ስለነበር ነው፡፡
(One stop center) በአንድ ተቋም ውስጥ ሁሉንም አገልግሎት የሚባለው አሰራር ተገዶ መደፈር የደረሰባቸው ሴቶች ከሌሎች ታካሚዎች ጋር ሳይደባለቁ ለብቻቸው ጉዳያቸውን ለባለሙያ የሚያስረዱበትና በውስጡ የስነልቡና እና አስፈላጊ የሆነውን ሕክምና፤የፖሊስ አገልግሎት፤ የአቃቤ ሕግ አገልግሎትን የሚያገኙበት ጥቃት ያደረሰባቸውም ሰው በፍትህ እንዲዳኝ ሁኔታዎች የሚመቻቹበት ስፍራ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች በአንድ ተቋም ውስጥ ሁሉንም አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን የ (One stop center) አሰራር አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ መስተዳድሮች ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቶአል፡፡  ይህ አምድም በአንድ ተቋም ስር በተማከለው አገልግሎት በሚሰጥበት ቦታ ያለውን ሁኔታ ሲዘግብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ለማስታወስ ያህልም በሐዋሳ፤አዲስ አበባ፤ባህርዳር፤መቀሌ፤በጅማ ሆስፒ ታሎች የነበረውን አሰራር እና በጊዜው በስፍራው ያገኘናቸውን ተጠቃሚዎች ሁኔታ ለአንባቢ አቅርበናል፡፡ ይህ አገልግሎት ለሴት ህጻናቱ አካላዊና ስነልቡናዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው እንዲሁም ጥፋተኛው ተገቢው የፍርድ ሂደት እንዲያገኝ የሚረዳ አሰራር ነው፡፡
የኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከአሁን ቀደም ያቋቋማቸው (One stop center) በአንድ ተቋም ውስጥ ለተጎዱ ሴቶች የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥባቸው አሰራር ወሲባዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች ሁኔታውን ከመግለጽ እና ወደ ህክምና እንዲሁም ፍትህ ከመሄድ ይልቅ በድብቅ ለከፋ የጤና መታወክና በዚያም ሰበብ ከተለያዩ ምክንያቶች ጋር በተያያዘ ለህል ፈት የሚዳረጉ የብዙዎችን ሕይወትና ጤንነት ለማትረፍ ነበር፡፡ ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ከብዙ ታካሚዎች ጋር የማይስተናገዱበትና ከመላው ህብረተሰብ የፍትህ አሰራር ሂደቶች ጋር በማያገናኝ ሁኔታ የሚሰሩ ስራዎች ባልዳበሩባቸው ስፍራዎች ሴት ልጆቹ አሁንም ለጉዳት መዳ ረጋቸው እሙን ነው፡፡
ዶ/ር ተስፋነህ ፍቅሬ እንደገለጹት የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (ESOG) ዋናው የስራ አቅጣጫ የስነተዋልዶ ጤና እንደመሆኑ ወሲባዊ ጥቃት የሚደርስባቸውን ሴቶች በተገቢው መንገድ አገልግሎቱን ለመስጠት ወደፊትም የሚችለውን ሁሉ የሚያደርግ ነው፡፡ በትግራይ የነበረው ማእከል በመቀሌ አይደር ሆስፒታል ብቻ የነበረ ሲሆን ቀደም ሲል በነበረውም አሰራር ወደሆስ ፒታሉ (One stop center) የሚመጡት ተገልጋዮች ከከተማዋ ውጭ ከሆኑ ሌሎች አካባ ቢዎች ጭምር እንደነበር አይዘነጋም፡፡
በአለም ላይ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ በሚያጋጥምበት ቦታ ሁሉ የመጀመሪያዎቹ ተጠ ቂዎች ሴቶችና ህጻናት መሆናቸው እሙን ነው፡፡ በመሆኑም በትግራይ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ብዙዎች ለወሲባዊ ጥቃት ተጋልጠው እንደነበር የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዚህም መረጃ ላይ በመመርኮዝ ከCenter for international reproductive health training በተገኘው ድጋፍ እንዲሁም ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር …ጤና ቢሮ እና በአይደር ሆስፒታል ካሉ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ጋር በመሆን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚጠቅመውን አንድ ተቋም (One stop center) መመስረት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት (One stop center) በትግራይ እንዲቋቋም የሚፈለገው በትግራይ ውስጥ  በሽሬ፤አድዋ፤አክሱም፤አዲግራት፤ማይጨው ላይ ነው፡፡ መቀሌ ላይም ከአሁን ቀደም በአይደር ሆስፒታል ተቋቁሞ የነበረውን (One stop center) መልሶ በማደራጀት አገልግሎቱ እንዲጀመር ከስምምነት ተደርሶአል፡፡
ስራውን ለመጀመር ከሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ስልጠና መስጠት ነው፡፡ GBV በሴ ቶች ላይ የሚደርሰውን ወሲባዊ ጥቃት በሚመለከት ስልጠናውን ለመስጠት የሚያግዝ በኢፊ ድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተዘጋጀ የስልጠና ዶክመንት ስላለ በዚያ መሰረት ከተጠቀሱት አካባቢ ዎች ለመጡ የጤና ባለሙያዎች በመቀሌ ስልጠና ተሰጥቶአል፡፡ ሰልጣኞቹ አንድ የጽን ስና ማህጸን ሐኪም…አንድ ጠቅላላ ሐኪም…አንድ ነርስ…አንድ ሚድዋይፍ ነርስ…ሳይካትሪ ነርስ…እና አንድ ማህበራዊ ሰራተኛ (Social Worker) በአጠቃላይ ከተጠቀሱት ቦታዎች ወደ 31 የሚሆኑ ባለሙያዎች ስልጠናውን ወስደዋል ፡፡ ዶ/ር ተስፋነህ ፍቅሬ እንደገለጹት በአሰራር ምክንያት ማለትም ለስራ የሚመደቡት ሐኪሞች በመለዋወጥ ላይ ስለነበሩ ከአድዋ የተወከሉ ሰልጣኞች አልነበሩም ፡፡ ስልጠናው የተሰጠው ከግንቦት 9-12/ድረስ ነበር፡፡
በትግራይ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ቀደም ሲል በጤና ተቋማቱ በቋሚነት ይሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች በአብዛኛው በአሁኑ ወቅት በቦታው የሉም፡፡ በዚህም ምክንያት  ህብረተሰቡ የጤና አገልግሎቱ እንዳይቋረጥበት መንግስት በወሰደው እርምጃ በየስድስት ወሩ ከተለያዩ ሆስፒታች እየተዋቀሩ እና ወደስፍራው በመሄድ እየተለዋወጡ እንዲሰሩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የጤና አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገናል፡፡ በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር እና በተባባሪ አካላት የሚሰጠውን ስልጠና አስቸጋሪ ቢያደርገውም በጊዜው በስራ ላይ ለነበሩት ባለሙያዎች ግን ተሰጥቶአል፡፡
ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች በአንድ ተቋም ለማገልገል የሚያስችለውን አሰራር በሚ መለከት የተሰጠው ስልጠና የመጀመሪያው ሲሆን ሌሎች ቀጣይ ስልጠናዎች እንደሚኖሩ ዶ/ር ተስፋነህ አብራርተዋል፡፡ ከስልጠናዎች ባሻገርም በአዲስ አበባ ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና እን ዲሰጥም ታቅዶአል፡፡ የአሰልጣኞች ስልጠና ከተሰጠ በሁዋላ ስልጠናው በመቀሌ ላይ ሳይወሰን አገልግሎቱ በሚሰጥበት ቦታ ድረስ በመሄድ ባለሙያዎቹን ለማብቃት እና በየስድስት ወሩ ለሚለዋወጡት ባለሙያዎችም ሁልጊዜ ስልጠናው እንዲዳረስ ለማድረግ ያስችላል፡፡ የፕሮጀክቱ አላማ በተቻለ መጠን በየጊዜው የሚለዋወጡ የህክምና ባለሙያዎችን በማብቃት የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ብቃት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው፡፡  
በትግራይ ወሲባዊ ጥቃት የሚደርስባቸውን ሴቶች በአንድ ተቋም ስር (One stop center) ሁሉንም አገልግሎት ማለትም ህክምናውን…የምክር አገልግሎቱን…ፍትሕን የማስከበር ስርአቱን …ወዘተ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል በሽሬ…አክሱም…አድዋ…አዲግራት… ማይጨው እና በመቀሌ አይደር ሆስፒታል የሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎችንና ማህበራዊ ሰራተኞችን ከማሰልጠን ባሸገር ፕሮጀክቱ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ገዝቶ በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር አማካኝነት ወደስፍራው ልኮአል፡፡
ተገዝተው የተላኩት እቃዎች አምቡላንሶች…በየሆስፒታሉ ተሰርተው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ጥራትና ጥንካሬ ያላቸው ተገጣጣሚ ቤቶች…. አልትራሳውንድና ሌሎች ጥቅም ላይ የሚውሉ የህክምና ቁሳቁሶች የተገዙበት ሁኔታ አለ፡፡ መድሀኒት እና የላቦራቶሪ እቃዎችም በሂደት እየተሟሉ ስራው እንዲጀመር በመመቻቸት ላይ ነው፡፡
በትግራይ ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸው የአካልና የአእምሮ ችግር ደርሶባቸው ወደተጠቀሱት ሆስ ፒታሎች (One stop center) የህክምናና የፍትህ አገልግሎት ለማግኘት የሚሄዱ ሴቶች የሚ ጠቀሙበት Dignity kit የሚባል በውስጡ ፎጣ…ቱታ…ለመጸዳጃ የሚያገለግል ፓድ… ማበ ጠሪያ…ጫማ የመሳሰሉትን መገልገያዎች የያዘ እሽግ በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (ESOG) ተገዝቶ ለየአንዳንድዋ ተጠቂ መስጠት በሚያስችል ሁኔታ ተዘጋጅቶ ወደ መቀሌ ተልኮአል፡፡ ይህ እሽግም እንደየአስፈላጊነቱ (One stop center) በአንድ ተቋም ሁሉ ንም አገልግሎት ለመስጠት በተመረጡት አካባቢዎች ባሉ ሆስፒታሎች ይከፋፈላል፡፡
ለጾታዊ ጥቃት አፋጣኝ ምላሽ (Emergency response to GBV) የተሰኘው ፕሮጀክት በት ግራይ ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የጀመራቸው ስራዎች ቀላል ባይሆኑም በተቻለ መጠን በብቃት ለመወጣት የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (ESOG) ድጋፍ በሚያደርጉ አካላት እየተጋዘ ይሰራል ብለዋል ዶ/ር ተስፋነህ ፍቅሬ የፕሮጀክቱ ማናጀር፡፡    

Read 13026 times