Saturday, 19 June 2021 18:13

‹‹ሄሎ ታክሲ›› የመጀመሪያውን ተንቀሳቃሽ የነዳጅ ማደል አገልግሎት ሊጀምር ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   50 የነዳጅ ማደያ መኪኖች በቅርቡ ይገባሉ ተብሏል 200 መኪኖችን ትናንት ለደንበኞቹ አስረክቧል

         ‹‹ሄሎ ታክሲ›› በአገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለውንና መኪኖች በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ ነዳጅ ቢያልቅባቸው ሊሞሉ የሚችሉበትን ተንቀሳቃሽ የነዳጅ ማደያ አገልግሎት ሊጀምር እንደሆነ ገለፀ፡፡ ከትናንት በስቲያ በመስቀል አደባባይ በተከናወነው ስነ-ሥርዓት የተንቀሳቃሽ ነዳጅ እደላ አገልግሎት የሚሰጡ መኪኖች ማሳያ ለህዝብ ዕይታ ቀርቧል፡፡
 በቅርቡም 50 ተንቀሳቃሽ ነዳጅ ማደያ መኪኖች ወደ አገር ውስጥ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡ ነዳጅ ማደያ መኪኖቹ ለደንበኞች አገልግሎት ከሰጡ በኋላ ለተከፈለው ሂሳብ ደረሰኝ ራሳቸው ቆርጠው የሚሰጡ መሆኑም ተነግሯል፡፡
#ሄሎ ታክሲ; በስካይ ላይት ሆቴል አዘጋጅቶት በነበረው ፕሮግራም ደረጃቸውን የጠበቁና ባለ ሰባት መቀመጫ 200 ዊሊንግ አውቶማቲክ የቱሪስት ታክሲዎችን ለደንበኞቹ ያስረከበ ሲሆን ከዚህ  በተጨማሪም ሶስት የቱሪስት አምቡላንሶችን ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡
በኮቪድ-19 በሽታ ስርጭትና በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ መኪኖቹን በወቅቱ ለደንበኞች ለማስረከብ እንቅፋት መፍጠራቸውን የተናገሩት የ#ሄሎ ታክሲ; ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዮሐንስ፤ ለተፈጠረው መዘግየት ደንበኞቻቸውን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
በዚሁ የርክክብና የማስተዋወቅ ፕሮግራም ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዴኤታ ወ/ሮ ቡዜና  አልከድር በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

Read 2026 times