Saturday, 19 June 2021 18:18

“ሀሺም ፋውንዴሽን” በይፋ ተመሰረተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

 የሁለተኛ ዓመት የማርኬቲንግ ተማሪ በሆነችውና በ20ዎቹ መጀመሪያ ዕድሜ ላይ በምትገኘው ወጣት ቀመር ሀሺም የተቋቋመው “ሀሺም ፋውንዴሽን” ባለፈው ረቡዕ ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል በይፋ ተመስርቶ ስራ ጀመረ፡፡ ወጣት ቀመር ለአባቷ መታሰቢያነት በስማቸው ያቋቋመችው ይህ ፋውንዴሽን ትኩረቱን በወጣቶች ላይ አድርጎ የሚሰራ ሲሆን በተለይ በወጣቱ ላይ ያለውን የአመለካከት መዛባት በመቅረፍ ወጣቱ የስራን ክቡርነት እንዲረዳና ስራ ሳይንቅ እንዲሰራ ለማድረግ ስልጠናዎችን በመስጠት የስራ ዕድል እንደሚፈጥርም ወጣት ቀመር ሀሺም ተናግራለች፡፡ በቦርድ የሚመራውና ከበጎ አድራጎትና  ማህበራት ኤጄንሲ ህጋዊ ሰውነት ያገኘው ፋውንዴሽኑ በአገራችን የወጣቱን አመለካከት በመቀየር ሥራ አጥነትን መቅረፍ የሚል መርህ የሚከተል ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያመጣ ስልጠና ለ3 ሺህ ወጣቶች ለመስጠትና እንደየዝንባሌያቸው የሙያ ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ እንደሚያስገባቸወም ወጣት ቀመር ገልፃለች፡፡
“ስራ አጥነት አዕምሯችን ውስጥ ብቻ ነው ያለው” የምትለው ቀመር፣ ይህ በስልጠና የሚስተካከል እንደሆነና ፋውንዴሽኑም እዚህ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ወጣቱን እንደሚያነቃ ገልፃለች፡፡ በምስረታው ላይ የፋውንዴሽኑ ቦርድ አባላት የወጣቷ ቤተሰቦች የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡



Read 13073 times