የኢዜማው አቶ ክቡር ገና ምርጫ ቦርድ ውጤት ሳይገልፅ ብልፅግናን “እንኳን ደስ አላችሁ! “ በማለት ፅፈዋል ።ጠ/ሚር አብይንም “የዚህ ምርጫ አሸናፊ “በማለት አሞግሰዋቸዋል።
ኢዜማ ምርጫ ካሸነፈ የአዲስ አበባ ከንቲባ ይሆናሉ ተብለው የተጠበቁት የኢዜማው አቶ ክቡር ገና ዛሬ በፌስቡካቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ይሄን ፅፈዋል;
“ ኢትዮጵያውያን አብይ አህመድን ጠ/ ሚ እንዲሆኑላቸው ወስነዋል። ጠ/ ሚሩም በውጭም በውስጥም ጠላቶች ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም ምርጫ እንዲከናወን አድርገዋል።ለዚህም ምስጋና ይገባቸዋል።”
“ጠ/ ሚሩ ኢትዮጵያን አንግብው ለህዝባቸው ተስፋን በመመገባቸው በብዙ መራጮች ልብ ገብተዋል“
“እኛ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠበቅብን ስራ አልሰራንም። ይሄን ለምን ሆነ? ብለን እራሳችን መጠየቅ፣ መፈተሽ፣ መወያየትና ለቀጣይ ስራዎች መዘጋጀት አለብን። ወጣት ፖለቲከኞችን ማምጣት አለብን። አምስት አመት በጣም ትንሽ ግዜ ናት!።”
“ግን ሀገሪቱን ለሚገዛት ፓርቲ ምክር አለኝ ።የሰፋውን የኑሮ ልዩነቱን ማቀራረብ ፣ድህነትን መቀነስ፣ የጤና አገልግሎትን ማስፋት፣ ስራ አጥነት ላይ ብዙ መስራት፣ ፍትህ ላይ መስራት፣ የተሻለ የንግድ ስርአትን ፈጥሮ ስራ ፈጣሪን እና ገቢን ማስፋት፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት፣ አንድነት ማምጣት ......” በማለት ፅፈዋል።
Published in
የሰሞኑ አጀንዳ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል