Sunday, 27 June 2021 18:51

“ዳና ሥር” ልቦለድ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

በደራሲ አንተነህ እሸቱ የተጻፈውና በሁለት ወጣቶች ፍቅር ላይ የሚያጠነጥነው “ዳና ሥር” ልቦለድ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሐፉ በዋናነት መቼቱን አዲስ አበባ ፣ ባሌ፣ ጎንደር፣ ጎርጎራ፣ ኳታርና ዱባይ አድር ሁለቱ ወጣት ተፋቃሪዎች መነጋገር ሲገባቸው ባመነጋገራቸውና በየራሳቸው መንገድ መጓዝ በመምረጣቸው የሚገጥማቸውን ፈተናና ውጣ ውረድ በመሳጭ ፍሰት የሚገልጽ ነው ተብሏል፡፡
በ326 ገፅ  የተቀነበበው ይህ መፅሐፍ በ160 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲው አንተነህ እሸቱ ከዚህ ቀደም “ጥርስ የገባ” የተሰኘ ረጅም ልቦለድና “ቀሚስ የጋረደው”፣ “እኔ ሀብታም”ና ከግድግዳው ጀርባ የተሰኙ አጫጭር ልቦለዶችን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡ ደራሲው በአሁኑ ሰዓት በኢኤስቲቪ አቦል ቲቪ ላይ የሚተላለፈው “ጨረቃ ፍቅር” ተከታታይ ድራማ ደራሲም ነው፡፡

Read 9636 times