Print this page
Sunday, 27 June 2021 18:55

“ሀገር በከዋክብት”

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል
በሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት በየወሩ የሚካሄደው “ሀገር በከዋክብት” የኪነ-ጥበብ ምሽት በዚህ ወር መሰናዶ “እኔም ለሀገሬ” በሚል ርዕስ ከነገ በስቲያ ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዕቱም ሙዚቃ፣ ግጥም ፣ አነቃቂ ንግግር፣ ወግ፣ የኮሜዲ ስራዎች እና ድንገቴ እንግዳ የሚኖር ሲሆን፣ ኢ/ር ዘለቀ ረዲ፣ ወዳጄነህ መሃረነ (ዶ/ር)፣ዮናስ ዘውዴ (ዶ/ር) ፣ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን፣ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፣ ኮሜዲያን ምትኩ ፈንቴ፣ ገጣሚኑ ከድር አሊ፣ በቃሉ ሙሉ፣ ማርታ ተስፋዬና ኪዳ የገጠር ልጅ (ቅዱስ) ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ የተባለ ሲሆን ድምፃዊ አስናቀ ገ/የስ ከልጁ ቢኒያም አስናቀ ገ/የስ ጋር የሙዚቃ ስራዎቻቸውን እደሚያቀርቡና የመግቢያ ዋጋውም 100 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡

Read 9405 times