Saturday, 26 June 2021 00:00

“የኢኮኖሚ መዋዠቅ እና የስትራጂ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በእውቁ ወጣት የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ሀሮን ጋንታ በጥልቅ ጥናትና ምርምር የተሰናዳውና ከኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት እስከ ብልጽግና ዘመን እየዋዠቀ የቀጠለውን የምጣኔ ሀብት ሁኔታ የሚተነትነው “የኢኮኖሚ መዋዠቅ እና የስትራቴጂ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ” የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሐፉ በዋናነት መንግስት ትኩረት ባልተሰጣቸው የኢኮኖሚ ስትራቴጂዎች፣ በመንግስት የተዝረከረከ አሰራርና የቁጥጥር መላላት፣ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ አገራት ሊተገበር ስለማይገባው የነፃ ገበያ ስትራቴጂ፣ በኢኮኖሚ መዋዠቅ ምክንያት ተጋላጭ ስለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ በባህልና በአስተሳሰብ ላይ ስለሚያደርሰው አሉታዊ ተፅዕኖና በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ጥልቅ ትንታኔ ይሰጣል፡፡
የምጣኔ ሃብት ባለሙያው በዋናነት ሊጤኑ ይገባቸዋል ያላቸውን ዘጠኝ ስትራቴጂዎችን በመለየት ትንታኔ የሰጠ ሲሆን፣ ኢኮኖሚው በመዋዠቁ ምክንያት በመጣው የዋጋ ግሽበት፣ የብር የመግዛ አቅም መውደቅና ይህን ተከትሎ ስለመጣው የሸቀጦች የዋጋ ንረትና ህዝቡን እያሰቃየ ስላለው የኑሮ ውድነትም ከበፊቶቹ ጊዜያት ጋር በማነጻጸር አስቀምጧል፡፡ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ያላቸውንም አመልክቷል፡፡ በ222 ገጽ ተቀንብቦ በ200 ብር እና በ15 ዶላር ለገበያ ያቀረበው መፅሐፉ በቅርቡ ለምርቃት እንደሚበቃም አቶ ሀሮን ጋንታ ገልጿል፡፡

Read 904 times