Print this page
Saturday, 03 July 2021 20:48

“ኢትዮጵያ” የባህል ውዝዋዜ ማሰልጠኛ በአዲስ አበባ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

መቀመጫውን ናዝሬት አዳማ ያደረገውና የመጀመሪውን (ቁጥር 1) አዳማ ከፍቶ በማሰልጠን ላይ የሚገኘው አፍሮ አርት አካዳሚ “ኢትዮጵያ” የባህል ውዝዋዜ ማሰልጠኛ ቁጥር 2 በአዲስ አበባ ቸርችል ጎዳና በሚገኘው ዳውን ታውን ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ መክፈቱን የአፍሮ አርት አካዳሚ መስራች ገጣሚና ተወዛዋዥ ኤፍሬም መኮንን (ኤፊ ማክ) ገለፀ፡፡
በዚህ የማሰልጠኛ ተቋም ሀገረ ሰብ ውዝዋዜዎች በሙሉ በስልጠናው የሚካተቱ ሲሆን በዘርፉ ልምድ ባካበቱ አሰልጣኞች በአጭር ጊዜ የውዝዋዜ ባለሙያ ሆኖ መውጣት እንደሚቻል ገጣሚና ፕሮፌሽናል ተወዛዋዡ ኤፍሬም መኮንን (ኤፊ ማክ) ገልጿል፡፡ በማሰልጠኛ ማዕከሉ ውዝዋዜን ከመሰልጠን ባለፈ የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ጤንነትን የመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጾ፣ ምዝገባ መጀመሩንና ከሳምንት በኋላ ስልጠና እንደሚጀምር ኤፍሬም መኮንን ጨምሮ ገልጿል፡፡

Read 2843 times