Monday, 05 July 2021 00:00

“በኢትዮጵያ እንታረቅ ቁጥር 2” የጥበብ ምሽት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በኢትዮጵ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስር በሚዘጋጀው “ዘመን” የኪነ-ጥበብ ምሽት የዚህ ወርመሰናዶ “በኢትዮጵያ እንታረቅ ቁጥር 2” በሚል መሪ ቃል ሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በአምባሳደር ሲኒማ ቤት ይካሄዳል፡፡ በዕለቱ ዲስኩር የሚያቀርቡት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ፣ እውቁ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ፣ ደራሲና የህክምና ባለሙያ ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድና አምባሳደር ታደለች ሃይለሚካኤል ሲሆኑ ገጣሚያኑ ዘውድ አክሊሉ፣ ጋዜጠኛ ወንድሙ ሃይሉ፣ ሳባ መኩሪያ፣ ሰለሞን  ሳህለ ትዕዛዙ፣ ዮሐንስ ኃ/ማርያም፣ አብርሃም አስቻለው፣ ረድኤት ሺባባውና ተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሽ) የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ በተጨማሪም ግጥም በውዝዋዜ ኤፍሬም መኮንን (ኤፊ ማክ) ሙዚቃ ናትናኤል ፍቃዱና ስዕል ደግሞ ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ የሚያቀርቡ ሲሆን የመግቢያ ዋጋውም 100 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡


Read 18280 times