Sunday, 11 July 2021 17:02

በሽረ ከተማ “ከ300 በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች ተገድለዋል”

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

ለውጡን ትደግፋላችሁ በሚል ግድያና እስር እየተፈፀመ ነው
                         
          የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት ከመቀሌና የትግራይ አካባቢዎች ለቆ መውጣቱን ተከትሎ፣ የታጣቂው የህወኃት ቡድን “ለውጡን ደግፋችኋል” በሚል ከ3 መቶ በላይ ኤርትራውያን ስደተኞችና የትግራይ ተወላጆችን እንደገደለ የመንግስት ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ትግራይን ከተቆጣጠረ ከ2 ሳምንት በላይ ያልሆነው ታጣቂ ሃይል፤  በተለይ በእንደርታና ራያ “ለውጡን ደግፈዋል” ያላቸውን እየገደለና በርካቶችን ወደ እስር ቤት እያጋዘ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በሽሬ ከተማ ተጠልለው ከሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች መካከልም ከ3 መቶ በላይ የሚሆኑ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በተለይ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ እንዲሁም “ቤተቦቻችሁ ለውጡን ይደግፋሉ” በሚል የተወነጀሉ ዜጎች ከፍተኛ የሠብሰአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ የጠቆሙት ምንጮች፤በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ዘረፋዎችና የስርቆት ወንጀሎች ፣መበራከታቸውንም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
አለማቀፉየሠብአዊ መብት ተሟጋች  ሂዩማን ራይትስ ዎች በበኩሌ፣ ትግራይን የተቆጣጠረው ታጣቂ ሃይል ለተጨማሪ ጦርነት ራሱን እያዘጋጀ መሆኑን ጠቁሞ ግድያዎችና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈፀሙ ነው የሚል ስጋት እንዳለው አመልክቷል፡፡

Read 9552 times