Sunday, 11 July 2021 18:31

“ሰው ሁን” ትርጉም መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በእውቁ  የንግድ አማካሪና ኢንቨስተር ቤድሮስ ኩሊያን የተፃፈውና በተርጓሚ አካሉ ቢረዳ ሰማ “ሰው ሁን” በሚል ወደ አማርኛ የተመለሰው የአስተሳሰብ ለውጥ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መፅሐፉ በውስጣችን ፀድቆ ፍሬ እያፈራ ያለውን የአረም ክምችት ነቅሎ በመጣል ድንቅ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችለንን እውቀትና የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያስታጥቅ ነው ተብሏል፡፡
በተለይ በመፅሐፉ መቅድም “ፍቃድ ሰጥቼሃለሁ” በሚል ርዕስ ስር በርካታ ጠቃሚና ለህይወት መርህ የሚሆኑ ጉዳዮች የተዘረዘሩ ሲሆን “የምትፈልገውን ዓይነት ህይወት በምትፈልገው ሁኔታ እንድትኖር ፈቃድ “ሰጥቼሃለሁ” የሚለውን ጨምሮ ይህን ለማሳካት ራስን ለስርዓት ማስገዛት፣ ግልፅና ፍቱን የሆነ የመረጃ ልውውጥ መፍጠር፣ የውሳኔ ሰው መሆን፣ ግንፍልተኝነትን ማስወገድ፣ የራዕይና የዓላማ ግልፅነትን መያዝና ዋንጫ የሚያስነሳ ቡድን መመስረት የሚሉት ሰው ለመሆን  በዋና መርህነት ተቀምጠዋል፡፡
በ212 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ፣ በ150 ብር እና በ18 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡”

Read 9852 times